መስከረም 24 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 45 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 15 ከአን. 9-17 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዳንኤል 1-3 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዳንኤል 2:17-30 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ በሰማይ የሚኖሩት የአምላክ ፍጥረታት የተደራጁ ናቸው?—rs ገጽ 280 ከአን. 1-3 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የአምላክን መንፈስ ላለማሳዘን መጠንቀቅ የምንችለው እንዴት ነው?—ኤፌ. 4:30 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
30 ደቂቃ፦ “የወጣቶች ጥያቄ—ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል? (ክፍል 2)” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ባለፈው ሳምንት በክፍል 1 ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች በአንድ ደቂቃ ውስጥ በመከለስ ክፍሉን ጀምር። ወጣቶች፣ በወጣትነት ዕድሜያቸው ይሖዋን ‘ለማሰብ’ ላደረጉት ጥረት ልባዊ ምስጋና በማቅረብ ክፍሉን ደምድም። (መክ. 12:1) ሕይወታቸውን በይሖዋ አገልግሎት ለማሳለፍ ባደረጉት ቁርጥ ውሳኔ እንዲገፉበት አበረታታቸው።
መዝሙር 51 እና ጸሎት