መስከረም 14 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 50 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 24 ከአን. 10-15 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 16-18 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 2 ነገሥት 17:12-18 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህ የተሻለ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?—nwt ገጽ 36 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አቤሜሌክ—ጭብጥ፦ ደፋር ሁኑ፤ የይሖዋን አገልጋዮችም አክብሩ—w12 5/1 ገጽ 31 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ ‘ምሥራቹን በተሟላ ሁኔታ መሥክሩ።’—ሥራ 20:24
10 ደቂቃ፦ “ምሥራቹን በተሟላ ሁኔታ መሥክሩ።” በወሩ ጭብጥ ላይ እንዲሁም ምሥክርነት መስጠት በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 1 ከአንቀጽ 1-11 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።—ሥራ 20:24
10 ደቂቃ፦ “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—በንግድ አካባቢዎች መመሥከር።” በውይይት የሚቀርብ። ሁለት ክፍል ያለው አጠር ያለ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። የመጀመሪያው፣ አንድ አስፋፊ የግለሰቡን ሁኔታ ሳያመዛዝን በንግድ ሥራ ላይ ለተሠማራ ሰው ለመመሥከር ሙከራ ሲያደርግ የሚያሳይ ይሆናል። ከዚያም አስፋፊው ሠርቶ ማሳያውን በድጋሚ ያቀርባል፤ በዚህ ጊዜ ግን አስፋፊው ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ ይጠቀማል። ሁለተኛው አቀራረብ ውጤታማ የሆነው ለምን እንደሆነ ሐሳብ እንዲሰጡ አድማጮችን ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ የክልል ስብሰባ ማሳሰቢያዎች። ይህ ክፍል በቪዲዮ የተደገፈ ሲሆን የጉባኤው ጸሐፊ በውይይት ያቀርበዋል። መጀመሪያ ላይ “የክልል ስብሰባ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም ጉባኤው ይበልጥ ሊሠራባቸው በሚገቡ ነጥቦች ላይ ትኩረት በማድረግ በቪዲዮው ላይ የታዩትን አንዳንድ ጎላ ያሉ ገጽታዎች ከልስ።
መዝሙር 96 እና ጸሎት