መስከረም 21 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 53 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 24 ከአን. 16-21 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 19-22 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 2 ነገሥት 20:12-21 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ናዖድ—ጭብጥ፦ ይሖዋ ሕዝቦቹን ይታደጋል—w04 3/15 ገጽ 29-31 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ “አሜን” የሚለው ቃል ምን ትርጉም አለው?—የቃላት መፍቻ፣ nwt ገጽ 1637 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ ‘ምሥራቹን በተሟላ ሁኔታ መሥክሩ።’—ሥራ 20:24
10 ደቂቃ፦ ያለፈው የአገልግሎት ዓመት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስል ነበር? በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። ባለፈው የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ያደረገውን እንቅስቃሴ ከልስ። ጉባኤው ባከናወናቸው መልካም ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግ ጉባኤውን አመስግን። በዚህ የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚችላቸውን አንድ ወይም ሁለት የአገልግሎት ዘርፎች ጥቀስ፤ ከዚያም በዚህ ረገድ ማሻሻያ ለማድረግ የሚረዱ ሐሳቦችን ተናገር።
10 ደቂቃ፦ በተሟላ ሁኔታ መመሥከር ውጤት ያስገኛል። በ2015 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ገጽ 54 አንቀጽ 1 እንዲሁም ከገጽ 56 አንቀጽ 2 እስከ ገጽ 57 አንቀጽ 1 እና ከገጽ 63 አንቀጽ 2 እስከ ገጽ 64 አንቀጽ 1 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። እያንዳንዱን ተሞክሮ ከተናገርክ በኋላ አድማጮች ምን ትምህርት እንዳገኙ ጠይቅ።
10 ደቂቃ፦ “በእምነታቸው ምሰሏቸው።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 81 እና ጸሎት