ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢሳይያስ 47-51
ይሖዋን መታዘዝ በረከት ያስገኛል
ይሖዋ በሕይወታችን ደስተኛ እንድንሆን ስለሚፈልግ ‘ልንሄድበት የሚገባን መንገድ’ የትኛው እንደሆነ ያሳየናል፤ ይህን የሚያደርገው ስለሚወደን ነው። እሱን የምንታዘዝ ከሆነ እኛው ራሳችን እንጠቀማለን።
“ሰላምህ እንደ ወንዝ”
ይሖዋ እንደ ወንዝ የማይቋረጥ ሰላም እንደምናገኝ ቃል ገብቶልናል
“ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ”
የጽድቅ ሥራችን ልክ እንደ ባሕር ሞገድ ሊቆጠር የማይችል ይሆናል