የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 178
  • መጥምቁ ዮሐንስ ማን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጥምቁ ዮሐንስ ማን ነው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • መጥምቁ ዮሐንስን ለየት የሚያደርገው ምንድን ነው?
  • የመጥምቁ ዮሐንስ ወላጆች እነማን ናቸው?
  • መጥምቁ ዮሐንስን ያስገደለው ማን ነው?
  • መጥምቁ ዮሐንስ እና ኢየሱስ ተቀናቃኝ ናቸው?
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ጥያቄ አቀረበ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ዮሐንስ እምነት ጎድሎት ነበርን?
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • መጥምቁ ዮሐንስ በእርግጥ በሕይወት የኖረ ሰው ነው?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 178
መጥምቁ ዮሐንስ አንድን ሰው ወንዝ ውስጥ ሲያጠምቅ።

መጥምቁ ዮሐንስ ማን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጥምቁ ዮሐንስ የአምላክ ነቢይ ነው። (ሉቃስ 1:76) በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም. የኖረ ሰው ነው፤ የተወለደውም ክርስቶስ ከመወለዱ ትንሽ ቀደም ብሎ ነው። አምላክ ለመሲሑ ወይም ለክርስቶስ መንገድ እንዲያዘጋጅ ተልእኮ ሰጥቶታል። ዮሐንስ የአምላክን መልእክት ለአይሁዳውያን ወገኖቹ በመስበክና ልባቸው ወደ አምላክ እንዲመለስ በማድረግ ይህን ተልእኮውን ተወጥቷል።—ማርቆስ 1:1-4፤ ሉቃስ 1:13, 16, 17

የዮሐንስ መልእክት፣ ቅን ልብ ያላቸው አድማጮቹ የናዝሬቱ ኢየሱስ ተስፋ የተደረገበት መሲሕ መሆኑን እንዲያውቁ ረድቷቸዋል። (ማቴዎስ 11:10) ዮሐንስ አድማጮቹን ከኃጢአታቸው ንስሐ እንዲገቡና የንስሐ ምልክት የሆነውን ጥምቀት እንዲጠመቁ አሳስቧቸዋል። (ሉቃስ 3:3-6) ዮሐንስ ብዙ ሰዎችን ስላጠመቀ “መጥምቁ” ወይም “አጥማቂው” ተብሎ ተጠርቷል። ካከናወናቸው ጥምቀቶች ሁሉ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የኢየሱስ ጥምቀትa ነው።—ማርቆስ 1:9

በዚህ ርዕስ ውስጥ፦

  • መጥምቁ ዮሐንስን ለየት የሚያደርገው ምንድን ነው?

  • የመጥምቁ ዮሐንስ ወላጆች እነማን ናቸው?

  • መጥምቁ ዮሐንስን ያስገደለው ማን ነው?

  • መጥምቁ ዮሐንስ እና ኢየሱስ ተቀናቃኝ ናቸው?

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዮሐንስ በሚለው ስም የተጠሩ ስንት ሰዎች አሉ?

መጥምቁ ዮሐንስን ለየት የሚያደርገው ምንድን ነው?

የሚያከናውነው ሥራ በትንቢት ተነግሯል፦ ዮሐንስ ያከናወነው የስብከት ሥራ የይሖዋን መልእክተኛ በተመለከተ የተነገረው ትንቢት እንዲፈጸም አድርጓል። (ሚልክያስ 3:1፤ ማቴዎስ 3:1-3) ‘ሰዎችን ለይሖዋ እንደሚያዘጋጅ’ አስቀድሞ የተነገረለት ሰው እሱ መሆኑን አሳይቷል፤ ይህን ያደረገው አይሁዳውያን ወገኖቹ የይሖዋ አምላክ ዋነኛ ወኪል የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን መልእክት እንዲቀበሉ መንገድ በማዘጋጀት ነው።—ሉቃስ 1:17

የሚታወስበት ታሪክ፦ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “ከሴት ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም፤ ሆኖም በመንግሥተ ሰማያት ዝቅተኛ የሆነው እንኳ ይበልጠዋል።” (ማቴዎስ 11:11) ዮሐንስ ነቢይ ብቻ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት የተነገረለት “መልእክተኛ” በመሆኑ ከእሱ በፊት ከተነሱት የአምላክ አገልጋዮች ሁሉ ይበልጣል ሊባል ይችላል። ኢየሱስ የተናገረው ሐሳብ ዮሐንስ በሰማይ በሚቋቋመው መንግሥት ነገሥታት ከሚሆኑት መካከል እንደማይሆንም ያሳያል።b ይህ ታማኝ ነቢይ የሞተው ክርስቶስ በሰማይ ሕይወት ማግኘት የሚቻልበትን መንገድ ከመክፈቱ በፊት ነው። (ዕብራውያን 10:19, 20) ይሁንና ዮሐንስ፣ ወደፊት ምድር ላይ ገነት ውስጥ ለዘላለም የመኖር አጋጣሚ ከሚያገኙት የአምላክ መንግሥት ተገዢዎች አንዱ ይሆናል።—መዝሙር 37:29፤ ሉቃስ 23:43

የመጥምቁ ዮሐንስ ወላጆች እነማን ናቸው?

የዮሐንስ ወላጆች፣ ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ የተባሉ ባልና ሚስት ናቸው። ዘካርያስ አይሁዳዊ ካህን ነው። ዮሐንስ የተወለደው በተአምር ነው፤ ምክንያቱም እናቱ መሃን ነበረች። በዚያ ላይ እሷና ዘካርያስ “በዕድሜ የገፉ ነበሩ።”—ሉቃስ 1:5-7, 13

መጥምቁ ዮሐንስን ያስገደለው ማን ነው?

ንጉሥ ሄሮድስ አንቲጳስ የዮሐንስን ራስ አስቆርጦታል። ዮሐንስን እንዲገድል ያነሳሳችው ሚስቱ ሄሮድያዳ ነች። ይህች ሴት ዮሐንስን ትጠላው ነበር፤ ምክንያቱም አይሁዳዊ እንደሆነ የሚናገረው ሄሮድስ ከሄሮድያዳ ጋር የመሠረተው ጋብቻ ከአይሁዳውያን ሕግ ጋር እንደሚጋጭ ዮሐንስ ይነግረው ነበር።—ማቴዎስ 14:1-12፤ ማርቆስ 6:16-19

መጥምቁ ዮሐንስ እና ኢየሱስ ተቀናቃኝ ናቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ ተቀናቃኝ እንደነበሩ የሚጠቁም ምንም ሐሳብ የለውም። (ዮሐንስ 3:25-30) እንዲያውም ዮሐንስ ተልእኮው ለመሲሑ መንገድ ማዘጋጀት እንጂ ከእሱ ጋር መፎካከር እንዳልሆነ በይፋ ተናግሯል። ዮሐንስ “እኔ በውኃ እያጠመቅኩ የመጣሁበት ምክንያት . . . እሱ ለእስራኤል እንዲገለጥ ነው” ብሏል። አክሎም “እሱም የአምላክ ልጅ [ነው]” በማለት መሥክሯል። (ዮሐንስ 1:26-34) በመሆኑም ዮሐንስ፣ ኢየሱስ በአገልግሎቱ ያገኘውን ስኬት ሲሰማ በጣም ተደስቷል።

a ኢየሱስ “ምንም ኃጢአት አልሠራም።” (1 ጴጥሮስ 2:21, 22) በመሆኑም ኢየሱስ የተጠመቀው ንስሐ መግባቱን ለማሳየት ሳይሆን የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ ራሱን እንዳቀረበ ለማሳየት ነው። የአምላክ ፈቃድ ሕይወቱን ለእኛ መስጠትንም ይጨምራል።—ዕብራውያን 10:7-10

b “ወደ ሰማይ የሚሄዱት እነማን ናቸው?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዮሐንስ በሚለው ስም የተጠሩ ስንት ሰዎች አሉ?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ዮሐንስ የሚባሉ አምስት ወንዶችን ይጠቅሳል።

  1. 1. መጥምቁ ዮሐንስ፣ የዘካርያስ እና የኤልሳቤጥ ልጅ።—ማርቆስ 1:4፤ ሉቃስ 1:57-60

  2. 2. ዮሐንስ፣ የሐዋርያው ጴጥሮስ አባት።—ዮሐንስ 1:42

  3. 3. ሐዋርያው ዮሐንስ፣ “የዘብዴዎስ ልጅ።” (ማቴዎስ 10:2) ይህ ሐዋርያ የዮሐንስ ወንጌልን፣ አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዮሐንስ የተባሉትን መልእክቶች እንዲሁም የራእይ መጽሐፍን ጽፏል።

  4. 4. ማርቆስ ተብሎም የሚጠራው ዮሐንስ፤ የማርቆስ ወንጌል ጸሐፊ ነው።—የሐዋርያት ሥራ 12:12

  5. 5. አይሁዳዊ ገዢ የሆነው ዮሐንስ፤ የካህናት አለቃ የሆነው የሐና ዘመድ ሊሆን ይችላል።—የሐዋርያት ሥራ 4:6

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ