የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 2/13 ገጽ 12-13
  • ፕላቶ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ፕላቶ
  • ንቁ!—2013
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ስለ ፕላቶ ማወቅ ለምን አስፈለገ?
  • የፕላቶ ትምህርት የተስፋፋው እንዴት ነው?
  • ጳውሎስና ፕላቶ ስለ ትንሣኤ የነበራቸው አመለካከት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ትምህርቱ ከአይሁድ፣ ከሕዝበ ክርስትናና ከእስልምና ሃይማኖቶች ጋር ተቀላቀለ
    ስንሞት ምን እንሆናለን?
  • ከሞት በኋላ ሕይወት—ሰዎች ምን ብለው ያምናሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • በትንሣኤ ላይ ያለህ እምነት ምን ያህል ጠንካራ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2013
g 2/13 ገጽ 12-13

የታሪክ መስኮት | ፕላቶ

ፕላቶ

ፕላቶ (ከ427-347 ዓ.ዓ. ገደማ) አረማዊ የግሪክ ፈላስፋ ነበር። የተወለደው አቴና ውስጥ ከአንድ የባላባት ቤተሰብ ሲሆን የከበርቴ ልጆች የሚማሩትን ትምህርት ተከታትሏል። በዘመኑ ታዋቂ የነበረው ሶቅራጥስ የተባለው ፈላስፋ እንዲሁም የፍልስፍናና የሒሳብ ሊቅ የሆነው የፓይታጎረስ ተከታዮች በፕላቶ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረዋል።

ፕላቶ በሜድትራንያን አካባቢ ከተዘዋወረና ሲሲሊ በተባለች የግሪክ ከተማ ውስጥ በምትገኘው በስራኩስ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ሲሳተፍ ከቆየ በኋላ ወደ አቴና ተመልሶ አካዳሚ በመባል የሚታወቀውን የፍልስፍናና የሳይንስ ትምህርት ቤት አቋቋመ። የመጀመሪያው የአውሮፓ ዩኒቨርሲቲ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ትምህርት ቤት የሒሳብና የፍልስፍና ምርምር ማዕከል በመሆን አገልግሏል።

ስለ ፕላቶ ማወቅ ለምን አስፈለገ?

የፕላቶ ትምህርት ክርስቲያን ነን የሚሉትን ጨምሮ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎች ሃይማኖታዊ እምነት ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል፤ እንዲያውም ከእነዚህ መካከል ብዙዎቹ የፕላቶ ትምህርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ እንደሆኑ ይሰማቸዋል። ከፕላቶ ትምህርቶች መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሰው ‘ሰው ሲሞት ከእሱ ተነጥላ የምትሄድ የማትሞት ነፍስ አለች’ የሚለው ነው።

“ፕላቶ እጅግ ይወዳቸው ከነበሩ ርዕሰ ጉዳዮች አንዱ የነፍስ ያለመሞት ባሕርይ ነው።”​—ቦዲ ኤንድ ሶል ኢን ኤንሸንት ፊሎሰፊ

ፕላቶ ከሞት በኋላ አለ ስለሚባለው ሕይወት የማወቅ ጥልቅ ፍላጎት ነበረው። ቦዲ ኤንድ ሶል ኢን ኤንሸንት ፊሎሰፊ (ሥጋና ነፍስ በጥንታዊው ፍልስፍና) የተባለው መጽሐፍ “ፕላቶ እጅግ ይወዳቸው ከነበሩ ርዕሰ ጉዳዮች አንዱ የነፍስ ያለመሞት ባሕርይ ነው” ይላል። ፕላቶ አንድ ሰው ሲሞት፣ ምድር ላይ ሳለ በነበረው አኗኗር መሠረት “ከሥጋው ተለይታ የምትሄደው ነፍስ ቅጣት ወይም ሽልማት” እንደምትቀበል በጥብቅ ያምን ነበር።a

የፕላቶ ትምህርት የተስፋፋው እንዴት ነው?

አካዳሚ የሚባለው የፕላቶ ትምህርት ቤት ሥራ ላይ በቆየባቸው ዘጠኝ መቶ ዓመታት ማለትም ከ387 ዓ.ዓ. እስከ 529 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት የፕላቶ ትምህርት በሰው ልጆች አስተሳሰብ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። በዚህ ወቅት የፕላቶ ፍልስፍና በግሪክና በሮም ግዛቶች ውስጥ ሰፊ ተቀባይነት አግኝቶ ነበር። አይሁዳዊ ፈላስፋ የነበረው የእስክንድርያው ፋይሎም ሆነ በርካታ የሕዝበ ክርስትና ሃይማኖታዊ መሪዎች የፕላቶን ፍልስፍና ተቀብለዋል። በዚህ ምክንያት ነፍስ አትሞትም የሚለውን ጨምሮ የአረማውያን የፍልስፍና ትምህርቶች ወደ አይሁድና ወደ ክርስትና እምነት ውስጥ ሰርገው ገቡ።

ዚ አንከር ባይብል ዲክሽነሪ እንዲህ ብሏል፦ “ሁሉም የክርስትና ሃይማኖታዊ ትምህርቶች በተወሰነ መጠንም ቢሆን በግሪክ ፍልስፍና፣ በዋነኛነት ደግሞ በፕላቶ ትምህርቶች ላይ የተመሠረቱ ናቸው። አንዳንድ የክርስትና ፈላስፎች ግን . . . ራሳቸውን ክርስቲያን አድርገው የሚቆጥሩ የፕላቶ ተከታዮች ናቸው።” እስቲ የሚከተሉትን የመረጃ ምንጮች አወዳድር።

ፕላቶ ምን ብሏል? “[አንድ ሰው ሲሞት] የማትሞት ነፍስ ብለን የምንጠራት የእያንዳንዳችን እውነተኛ ማንነት፣ አማልክት ወደሚገኙበት በመሄድ . . . በዚያ ለፍርድ ትቆማለች፤ ይህ ደግሞ ጥሩ ሰዎች በመተማመን፣ ክፉ ሰዎች ደግሞ በከፍተኛ ፍርሃት የሚጠብቁት ነገር ነው።”—ፕላቶ፣ ሎውስ (12ኛ ጥራዝ)

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ነፍስ፣ አንድን ግለሰብ ወይም ሕይወቱን ታመለክታለች። እንስሳት ሳይቀሩ ነፍሳት ናቸው። በሞት ጊዜ ነፍስ ከሕልውና ውጭ ትሆናለች።b የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ልብ በል፦

  • “የመጀመሪያው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ።”—1 ቆሮንቶስ 15:45

  • “ሁለተኛውም በሳህኑ ውስጥ ያለውን ወደ ባሕር አፈሰሰው። ባሕሩም እንደሞተ ሰው ደም ሆነ፤ ሕያው ነፍስ ሁሉ፣ አዎ፣ በባሕር ውስጥ ያለ ነገር ሁሉ ሞተ።”—ራእይ 16:3

  • “ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአል።”—ኢሳይያስ 53:12 የ1954 ትርጉም

  • “ኀጢአት የምትሠራ ነፍስ እርሷ ትሞታለች።”—ሕዝቅኤል 18:4

[ሥዕል]

ከዚህ በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው መጽሐፍ ቅዱስ ነፍስ ከሥጋ ተለይታ በሕይወት እንደምትኖር አያስተምርም። ስለዚህ ‘እምነቴ የተመሠረተው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ነው ወይስ በፕላቶ ፍልስፍና?’ ብለህ ራስህን ጠይቅ።

a ነፍስ አትሞትም የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ ያስፋፋው ፕላቶ ቢሆንም ጽንሰ ሐሳቡን ለመቀበል የመጀመሪያው ሰው አልነበረም። ይህ ጽንሰ ሐሳብ በተለያየ መልክ ይገለጽ እንጂ የግብፃውያንንና የባቢሎናውያንን ሃይማኖቶች ጨምሮ በተለያዩ አረማዊ ሃይማኖቶች ውስጥ ሲታመንበት በርካታ ዘመናት አልፈዋል።

b መጽሐፍ ቅዱስ ሙታን ያሉበት ሁኔታ ከእንቅልፍ ጋር እንደሚመሳሰልና በትንሣኤ የሚነቁበትን ጊዜ እንደሚጠባበቁ ይናገራል። (መክብብ 9:5፤ ዮሐንስ 11:11-14፤ የሐዋርያት ሥራ 24:15) ከዚህ በተቃራኒ ግን ነፍስ ዘላለማዊ ብትሆን ኖሮ ስለማትሞት ትንሣኤ አያስፈልጋትም ነበር ማለት ነው።

“ከሞት በኋላም ነፍስ በሕይወት ትቀጥላለች የሚለው ሐሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ሰፍሮ አይገኝም።”—ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒዲያ

“ነፍስ አትሞትም የሚለው ግልጽና ጠንካራ የሆነ እምነት የተመሠረተው . . . እንዲሁም ይህ ትምህርት ከአይሁድና ከክርስትና እምነት የመሠረት ድንጋዮች አንዱ የሆነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን በኋላ ነው።”—ኢንሳይክሎፒዲያ ጁዳይካ

“ከሞት በኋላ ነፍስ በሕይወት መኖሯን ትቀጥላለች የሚለው እምነት የተመሠረተው . . . በፍልስፍና አሊያም በሃይማኖታዊ መላምት ላይ ነው። እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በየትኛውም ቦታ በግልጽ ሰፍሮ አይገኝም።”—ዘ ጁዊሽ ኢንሳይክሎፒዲያ

አጭር መረጃ

  • ፕላቶ በምዕራቡ ዓለም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ካሳደሩ ፈላስፎች አንዱ እንደሆነ ይታመናል።

  • በወጣትነት ዕድሜው ወደ ፖለቲካ ቢያዘነብልም የፖለቲካው ዓለም ተስፋ አስቆራጭ ሆኖበት ነበር።

  • ቆየት ብሎም የሥነ ምግባር ደንብን፣ ፍትሕን፣ እውቀትን፣ ልከኝነትን፣ ነፍስን፣ ጀግንነትንና ሃይማኖተኛ መሆንን በተመለከተ ጽፏል።

  • ከፕላቶ ተማሪዎች መካከል ትልቅ እውቅና ያገኘው አርስቶትል ሲሆን እሱም አስተማሪ፣ ፈላስፋና የሳይንስ ሊቅ ነበር።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ