የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 9/14 ገጽ 14-15
  • ስፔን ሞሪስኮዎችን አባረረች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ስፔን ሞሪስኮዎችን አባረረች
  • ንቁ!—2014
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በግዳጅ ሃይማኖትን ማስለወጥ
  • “ጥሩ ክርስቲያንም ሆነ ታማኝ ተገዢ” አልሆኑም
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2014
  • በመካከለኛው ዘመን በስፔን የአምላክን ቃል ማሳወቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • አልሃምብራ—በግራናዳ የሚገኝ የሙስሊሞች ዕንቁ
    ንቁ!—2006
  • የስፓንኛ መጽሐፍ ቅዱስ ያደረገው የሕልውና ተጋድሎ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2014
g 9/14 ገጽ 14-15
ሞሪስኮዎች ከስፔን ሲባረሩ

የታሪክ መስኮት

ስፔን ሞሪስኮዎችን አባረረች

ስፔን ይህን አሳዛኝ ድርጊት የፈጸመችው በዋነኝነት በቤተ ክርስቲያኒቱ ገፋፊነት እንደሆነ ይነገራል። ይህ ልታውቀው የሚገባ ታሪክ ነው።

የስፔን ንጉሣዊ መንግሥት ስፔንን በአንድ ሕግ የምትተዳደር ክርስቲያን አገር ማድረግ ፈለገ። ሞሪስኮዎች እንደ አረመኔ ይቆጠሩ ስለነበረ የእነሱ መኖር በአምላክ ዘንድ እጅግ የተጠላ ነገር እንደሆነ ይታሰብ ነበር። ከበርካታ ዓመታት በኋላ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አንድ ውሳኔ ላይ ተደረሰ። መፍትሔው ምን ነበር? ሞሪስኮዎችን ማባረር!a

በግዳጅ ሃይማኖትን ማስለወጥ

ሙዴሃር ተብለው የሚጠሩት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው በስፔን የሚኖሩ ሙስሊም ሙሮች በካቶሊኮች ቁጥጥር ሥር በነበሩ አካባቢዎች ውስጥ በአንጻራዊ ሁኔታ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በሰላም ኖረዋል። ለተወሰነ ጊዜም በአንዳንድ አካባቢዎች የራሳቸውን ሕግ፣ ባሕልና ሃይማኖት እንዲከተሉ ሕጋዊ መብት ተሰጥቷቸው ነበር።

በ1492 ግን ዳግማዊ ፈርዲናንድ እና ኢዛቤላ የሚባሉ ካቶሊክ ነገሥታት በአይቤርያ ባሕረ ገብ መሬት በሙስሊሞች ቁጥጥር ሥር የቀረችውን ግራናዳ የተባለችውን የመጨረሻ ግዛት ወርረው ያዙ። ግዛቲቱ እጇን በሰጠችበት ወቅት የተደረገው ስምምነት በዚያ ይኖር ለነበረው የሙር ሕዝብ የሙዴሃሮች ዓይነት መብት የሚሰጥ ነበር። ብዙም ሳይቆይ ግን ካቶሊክ መሪዎች በግዛታቸው ሥር የሚኖሩ ሙስሊሞች ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ የሚያሳድሩት ጫናና ስደት እየተባባሰ ሄደ። ሙሮች የሚፈጸምባቸው በደል ቀደም ሲል የተደረገውን ስምምነት የሚጥስ መሆኑን በመቃወም በ1499 ዓመፁ። በዚህ ጊዜ የመንግሥት ወታደሮች ዓመፁን አዳፈኑት፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ግን በየአካባቢው የሚኖሩ ሙስሊሞች ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ ካልሆነም አገር ለቀው እንዲወጡ ተገደዱ። ስፔናውያን፣ ሃይማኖታቸውን ቀይረው በስፔን የቀሩትን ሙስሊሞች ሞሪስኮ ብለው ጠሯቸው።

“ጥሩ ክርስቲያንም ሆነ ታማኝ ተገዢ” አልሆኑም

በ1526 የእስልምና ሃይማኖት በመላው ስፔን ታገደ፤ ያም ቢሆን ብዙ ሞሪስኮዎች ሃይማኖታቸውን በሚስጥር ያካሂዱ ነበር። በአብዛኛው ባሕላቸውን ጠብቀው ኖረዋል።

መጀመሪያ ላይ የሞሪስኮዎች የይስሙላ ካቶሊክነት ችላ ተብሎ ነበር። ደግሞም በዕደ ጥበብ፣ በጉልበት ሥራና በግብር ከፋይነት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር። ሆኖም በአጠቃላይ ሲታይ ሞሪስኮዎች ከሌላው ሕዝብ ጋር ለመቀላቀል እምቢተኛ መሆናቸው እንዲጠሉ አደረጋቸው፤ በዚህም የተነሳ በመንግሥትም ሆነ በተራው ሕዝብ መድልዎ ይፈጸምባቸው ጀመር። እንዲህ ያለው መሠረተ ቢስ ጥላቻ እንዲፋፋም ያደረገው ቤተ ክርስቲያኒቱ፣ ሞሪስኮዎች ሃይማኖታቸውን የለወጡት ከልባቸው ስለ መሆኑ ያደረባት ጥርጣሬ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ ሳይሆን አይቀርም።

ብዙም ሳይቆይ በቸልታ ማለፍ ቀረና ማስገደድ ተጀመረ። በ1567 ዳግማዊ ፊሊፕ የተባለው ንጉሥ የሞሪስኮዎችን ቋንቋ፣ አለባበስ፣ ባሕልና ወግ የሚያግድ ሕግ አወጣ። ይህ እርምጃ በድጋሚ ዓመፅ እንዲቀሰቀስና ደም መፋሰስ እንዲከሰት አደረገ።

በደረሰባቸው ከፍተኛ ሥቃይ የተነሳ ወደ 300,000 ገደማ የሚሆኑ ሞሪስኮዎች ከስፔን ለመውጣት እንደተገደዱ ይገመታል

የታሪክ ምሁራን እንደገለጹት የስፔን ገዢዎች “ሞሪስኮዎች ጥሩ ክርስቲያንም ሆነ ታማኝ ተገዢ እንዳልሆኑ” ተሰማቸው። በዚህ የተነሳ ከስፔን ጠላቶች ማለትም ከባሕር ላይ ወንበዴዎች፣ ከፈረንሳይ ፕሮቴስታንቶችና ከቱርኮች ጋር በማሴር ስፔንን ለወረራ እንዳጋለጡ ክስ ቀረበባቸው። ሞሪስኮዎች ውሎ አድሮ አገር መክዳታቸው አይቀርም የሚለው ፍርሃትና ለእነሱ የነበረው መሠረተ ቢስ ጥላቻ ከሌሎች ምክንያቶች ጋር ተዳምሮ ሳልሳዊ ፊሊፕ በ1609 ከአገር እንዲባረሩ ወሰነ።b በቀጣዮቹ ዓመታት ሞሪስኮዎች ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች ስደት ደረሰባቸው። በዚህ አሳፋሪ መንገድ ስፔን ሙሉ በሙሉ የካቶሊክ አገር ሆነች።

a ሞሪስኮ ማለት በስፓንኛ “ትንሽ ሙሮች” ማለት ነው። የታሪክ ምሁራን ይህን ቃል የሚጠቀሙት እንደ ስድብ ሳይሆን የመጨረሻው ሙስሊም መንግሥት በ1492 ከወደቀ በኋላ ወደ ካቶሊክነት ተለውጠው በአይቤርያ ባሕረ ገብ ምድር የቀሩትን ሙስሊም የነበሩ ሰዎች ለማመልከት ነው።

b በተጨማሪም የታሪክ ምሁራን ከስፔን ገዢዎች መካከል ቢያንስ አንዱ የሞሪስኮዎችን ንብረት በመውሰድ ብዙ ጥቅም እንዳገኘ ይገምታሉ።

አጭር መረጃ

  • በስምንተኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ የሰሜን አፍሪካና የአረብ ሙስሊሞች፣ በአሁኑ ጊዜ ስፔንና ፖርቱጋል የሚባሉት አገሮች የሚገኙበትን አብዛኛውን የአይቤርያን ባሕረ ገብ መሬት ግዛታቸው አድርገው ያዙ።

  • የካቶሊክ ሠራዊቶች ቀስ በቀስ ግዛታቸውን ያስመለሱ ሲሆን በ1492 በግራናዳ አካባቢ የሚገኘውን የመጨረሻውን የሙሮች ግዛት በወሰዱበት ወቅት ወረራቸውን አጠናቀዋል።

  • በ1492 ንጉሥ ፈርዲናንድና ንግሥት ኢዛቤላ ወደ ካቶሊክ ለመለወጥ ፈቃደኛ ያልሆኑ አይሁዳውያንን በሙሉ ከግዛታቸው አባረሩ። በ1500ዎቹ ዓመታት ሃይማኖታቸውን በለወጡ ሙስሊሞችና በዘሮቻቸው ላይ ስደት የደረሰባቸው ከመሆኑም ሌላ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። ከ1609 እስከ 1614 ባሉት ዓመታት ሞሪስኮዎች ማለትም ወደ ክርስትና የተቀየሩት ሙስሊሞች ከአገር ተባረሩ።

  • በደረሰባቸው ከፍተኛ ሥቃይ የተነሳ ወደ 300,000 ገደማ የሚሆኑ ሞሪስኮዎች ከስፔን ለመውጣት እንደተገደዱ ይገመታል። ቢያንስ 10,000 የሚያህሉ ሰዎች ከአገር ለመውጣት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሕይወታቸውን አጥተዋል።

“ንጹሕ” የካቶሊክ እምነት በመላው አገር!

የቫሌንሲያ ሊቀ ጳጳሳት የሆነው ህዋን ዴ ሪቤራ የሞሪስኮዎችን ከአገር መባረር ሙሉ በሙሉ ደግፏል

የቫሌንሲያ ሊቀ ጳጳሳት የሆነው ህዋን ዴ ሪቤራ የሞሪስኮዎችን ከአገር መባረር ሙሉ በሙሉ ደግፏል

ስፔን ከሞሪስኮዎች የምታገኘውን የሠራተኛ ኃይል በማጣቷ የኢኮኖሚ ኪሳራ እንደደረሰባት ጥርጥር የለውም። ያም ቢሆን እነዚህ ሰዎች በመባረራቸው አገሪቱ ፈንጥዛለች። አብዛኞቹ ስፔናውያን፣ አስመሳይ ሃይማኖተኛ ተደርገው የሚታዩት ሞሪስኮዎች በአገሪቱ መኖራቸው “ሕዝቡን ለረጅም ጊዜ ሲያበሳጭ እንደቆየና አገሪቱን እንዳዋረደ” ያስቡ እንደነበር የታሪክ መጻሕፍት ይናገራሉ። አሁን ለብስጭታቸው ምክንያት የሆነው ነገር ተወገደላቸው። በመሆኑም “ንጹሕ” የካቶሊክ እምነት በአገራቸው በመስፈኑ የስፔን መሪዎች፣ ጠቅላላው ሕዝብና ቤተ ክርስቲያኒቱ ተደሰቱ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ