ቅዳሜ
“ቆሻሻና እድፍ ሳይኖርባችሁ በሰላም [ተገኙ]”—2 ጴጥሮስ 3:14
ጠዋት
3:20 የሙዚቃ ቪዲዮ
3:30 መዝሙር ቁ. 58 እና ጸሎት
3:40 ሲምፖዚየም፦ “የሰላምን ምሥራች” ለማወጅ ዝግጁ ሁኑ
• ቅንዓታችሁን ይዛችሁ ቀጥሉ (ሮም 1:14, 15)
• ጥሩ ዝግጅት አድርጉ (2 ጢሞቴዎስ 2:15)
• ቅድሚያውን ውሰዱ (ዮሐንስ 4:6, 7, 9, 25, 26)
• ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተከታትላችሁ እርዱ (1 ቆሮንቶስ 3:6)
• ጥናቶች ወደ ጉልምስና እንዲደርሱ እርዱ (ዕብራውያን 6:1)
4:40 ወጣቶች—ወደ ሰላም የሚወስደውን ጎዳና ምረጡ! (ማቴዎስ 6:33፤ ሉቃስ 7:35፤ ያዕቆብ 1:4)
5:00 መዝሙር ቁ. 135 እና ማስታወቂያዎች
5:10 ቪዲዮ፦ ወንድሞቻችን ሰላማቸውን ጠብቀው እየኖሩ ያሉት እንዴት ነው?
• ተቃውሞ ቢደርስባቸውም
• ሕመም ቢያጋጥማቸውም
• የኢኮኖሚ ችግር ቢኖርባቸውም
• የተፈጥሮ አደጋ ቢያጋጥማቸውም
5:45 የጥምቀት ንግግር፦ “በሰላም መንገድ” ላይ መጓዛችሁን ቀጥሉ (ሉቃስ 1:79፤ 2 ቆሮንቶስ 4:16-18፤ 13:11)
6:15 መዝሙር ቁ. 54 እና የምሳ እረፍት
ከሰዓት በኋላ
7:35 የሙዚቃ ቪዲዮ
7:45 መዝሙር ቁ. 29
7:50 ሲምፖዚየም፦ ሰላም የሚያደፈርሱ ነገሮችን ‘አውልቃችሁ ጣሉ’
• ተገቢ ያልሆነ ኩራት (ኤፌሶን 4:22፤ 1 ቆሮንቶስ 4:7)
• ቅናት (ፊልጵስዩስ 2:3, 4)
• ውሸት (ኤፌሶን 4:25)
• ጎጂ ሐሜት (ምሳሌ 15:28)
• በቁጣ መገንፈል (ያዕቆብ 1:19)
8:45 መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድራማ፦ ይሖዋ በሰላም መንገድ ላይ ይመራናል—ክፍል 1 (ኢሳይያስ 48:17, 18)
9:15 መዝሙር ቁ. 130 እና ማስታወቂያዎች
9:25 ሲምፖዚየም፦ ‘ሰላምን ፈልጉ፤ ተከተሉትም’
• ለቁጣ ባለመቸኮል (ምሳሌ 19:11፤ መክብብ 7:9፤ 1 ጴጥሮስ 3:11)
• ይቅርታ በመጠየቅ (ማቴዎስ 5:23, 24፤ የሐዋርያት ሥራ 23:3-5)
• በነፃ ይቅር በማለት (ቆላስይስ 3:13)
• ስጦታ የሆነውን አንደበታችንን በጥበብ በመጠቀም (ምሳሌ 12:18፤ 18:21)
10:15 ‘አንድ ላይ የሚያስተሳስረንን የሰላም ማሰሪያ’ ጠብቁ! (ኤፌሶን 4:1-6)
10:50 መዝሙር ቁ. 113 እና የመደምደሚያ ጸሎት