ተመላልሶ መጠየቅ
ምዕራፍ 7
አለመታከት
መሠረታዊ ሥርዓት፦ “[ምሥራቹን] ያለማሰለስ ማስተማራቸውንና ማወጃቸውን ቀጠሉ።”—ሥራ 5:42
ጳውሎስ ምን አድርጓል?
1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም የሐዋርያት ሥራ 19:8-10ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦
ሀ. ጳውሎስ፣ አንዳንዶች ቢቃወሙትም ምሥራቹን ሳይታክት እንደሰበከ የሚያሳየው ምንድን ነው?
ለ. ጳውሎስ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ያስተማረው በየስንት ጊዜው ነው? ለምን ያህል ጊዜስ ይህን ሲያደርግ ቆይቷል?
ከጳውሎስ ምን እንማራለን?
2. ውጤታማ ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግና ጥናት ማስጀመር ጊዜና ጥረት ይጠይቃል።
ጳውሎስን ምሰል
3. ፕሮግራምህን ከግለሰቡ ፕሮግራም ጋር አስማማ። ራስህን ‘ግለሰቡ ለመወያየት ይበልጥ የሚመቸው መቼና የት ነው?’ ብለህ ጠይቅ። ጊዜው ለአንተ አመቺ ባይሆንም እንኳ ፕሮግራምህን ለማስተካከል ጥረት አድርግ።
4. ቀጠሮ ያዝ። በእያንዳንዱ ውይይት መጨረሻ ላይ በቀጣዩ ጊዜ የምትገናኙበትን ቁርጥ ያለ ቀጠሮ ያዙ። ቀጠሮህን አክብር።
5. አዎንታዊ ሁን። ግለሰቡን በተደጋጋሚ ቤት ስላጣኸው ወይም ሥራ ስለሚበዛበት ብቻ ‘ፍላጎት የለውም’ ብለህ አትደምድም። (1 ቆሮ. 13:4, 7) ሳትታክት መርዳትህ አስፈላጊ ነው፤ ያም ቢሆን ጊዜህ እንዳይባክንብህ ተጠንቀቅ።—1 ቆሮ. 9:26