የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 1/1 ገጽ 23
  • “የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘አምላክ ለሰው ፊት አያደላም’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • መልካም ሥራዎች ይሖዋን ያስከብራሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ይሖዋን ለማገልገል ቆርጠዋል!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • እንደምትወጂያቸው ንገሪያቸው
    የይሖዋ ምሥክሮች ተሞክሮዎች
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 1/1 ገጽ 23

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

“የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ”

የክርስቲያን ጉባኤ ከተቋቋመ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የአባላቱ ቁጥር ከ120 ተነሥቶ ወደ 3,000 አደገ። (ሥራ 1:15፤ 2:41) መጽሐፍ ቅዱስ “የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፣ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቁጥር እጅግ እየበዛ ሄደ” በማለት ይገልጻል። (ሥራ 6:7) ከጥቂት ዓመታት በኋላ ይህ አዲስ የተቋቋመ ጉባኤ በአፍሪካ፣ በእስያና በአውሮፓ የሚገኙ ክርስቲያኖችን ያቀፈ ዓለም አቀፍ ድርጅት ሆነ።

በዛሬው ጊዜ የሚገኘው የክርስቲያን ጉባኤም ተመሳሳይ የሆነ ፈጣን እድገት በማድረግ ላይ ነው። ለምሳሌ ያህል በሜክሲኮ ውስጥ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ቁጥር በአምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ130,000 ወደ 443,640 ከፍ ብሏል! በ1995 በሜክሲኮ ውስጥ ከ59 ሰዎች አንዱ የይሖዋ ምሥክሮች ባከበሩት የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ ተገኝቷል። ሆኖም የሚከተለው ተሞክሮ እንደሚያሳየው በዚያች አገር ውስጥ መንፈሳዊ መከር የመሰብሰቡ ሥራ ገና አልተጠናቀቀም።—ማቴዎስ 9:37, 38

ቺያፓስ በተባለች አንድ ከተማ ውስጥ ለ20 ዓመታት ያህል ምሥራቹ ቢሰበክም አንድም ሰው ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማድረግ አይፈልግም ነበር። አብዛኞቹ የከተማዋ ነዋሪዎች ይህን ያደረጉት በኃይለኛነቱ የሚታወቀውን ሰው ፈርተው እንደ ነበር ግልጽ ነው። ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ሲያጠኑ ቢያገኛቸው የሚደርስባቸውን ነገር ይፈሩ ነበር።

ወደዚያ አካባቢ የመጡ ሁለት ደፋር የይሖዋ ምሥክሮች በቀጥታ ከሰውዬው ጋር በመነጋገር ችግሩን ለመፍታት ወሰኑ። ሰውዬው ቤት ሄደው በሩን ሲያንኳኩ ሚስትየዋ ከፈተችላቸውና መልእክታቸውን በጥሞና አዳመጠች። በተለይ መጽሐፍ ቅዱስ በምድር ላይ በገነት ስለ መኖር የሚናገረው ነገር ፍላጎት አሳደረባት። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን ካጠናች ባሏ ከባድ ችግር እንደሚያደርስባት ነገረቻቸው። ምሥክሮቹ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን በጥንቃቄ እስካልመረመረች ድረስ አምላክን ማገልገልና በምድር ላይ ለዘላለም መኖር የሚቻልበትን መንገድ ልታውቅ እንደማትችል ገለጹላት። መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ተስማማች።

እንደተጠበቀው ባሏ በውሳኔዋ አልተደሰተም። ምንም እንኳ ሌሎች ጉዳዮችን ለማከናወን እንድትጠቀምበት ቢፈቅድላትም በመኪናዋ ወደ ክርስቲያናዊ ስብሰባዎች እንዳትሄድ ከለከላት። ባሏ ቢቃወማትም እንኳ ካለችበት ቦታ 10 ኪሎ ሜትር ርቆ ወደሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ ዘወትር ትሄድ ነበር። ወዲያው በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ሰዎች ድፍረቷንና ቆራጥነቷን ተመለከቱ። የይሖዋ ምሥክሮች ወደ ቤታቸው ሲመጡ ማዳመጥ ጀመሩ። እንዲያውም አንዳንዶች ከሴትየዋ ጋር ወደ ስብሰባዎቹ መሄድ ጀመሩ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ በዚያች ከተማ ውስጥ የይሖዋ ምሥክሮች 20 የሚያህሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን መምራት ጀመሩ!

በተጨማሪም የዚህች ሴት ጓደኛ ባሏ ቢቃወማትም መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ወሰነች። የሚገርመው ይህን እንድታደርግ ያበረታታት የመጀመሪያይቱ ሴት ባል ነው። ይህ ሰው ባልዋን ካነጋገረው በኋላ ተቃውሞው አቆመ። ስለዚህ ከ20 ዓመታት በኋላ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ዘር ማቆጥቆጥ ጀመረ። በአሁኑ ወቅት ምሥራቹን በማስፋፋት ላይ የሚገኙትን እነዚህን ሁለት ሴቶች ጨምሮ ከ15 ሰዎች በላይ መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ላይ ሲሆኑ በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይም ይገኛሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ