የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 2/15 ገጽ 3-4
  • ብዙ ሥቃይና መከራ አለ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ብዙ ሥቃይና መከራ አለ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “በመከራና በሐዘን” የተሞላ
  • የአምላክ ዓላማ ነበርን?
  • ሥቃይና መከራ የማይኖርበት ጊዜ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ጥያቄ 3፦ አምላክ መከራ እንዲደርስብኝ የሚፈቅደው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?
    አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 2/15 ገጽ 3-4

ብዙ ሥቃይና መከራ አለ

“ይህ ሁሉ በጣም አስከፊ የሆነ ሥቃይና መከራ በተናጥልም ሆነ በጅምላ በሰዎች ላይ ሊደርስ የቻለው ለምንድን ነው . . . ? አምላክ ሁሉንም ነገር የሚያደርገው በዓላማ ነው ተብሎ ቢታመንም በዚህች ዓለም ውስጥ ብዙ ትርጉም የለሽ ነገሮች ይከሰታሉ፣ ብዙ ትርጉም የለሽ ሥቃይና መከራ እንዲሁም ኃጢአት አለ። ምናልባት ይሄ አምላክ ኒትሽ የተባለው ሰው አምባገነን፣ አስመሳይ፣ አጭበርባሪና ነፍሰ ገዳይ በማለት የከሰሰው ዓይነት አምላክ ይሆን?”​— On Being a Christian, በሃንስ ኩንግ

የካቶሊክ ሃይማኖት ምሁር የሆኑት ሃንስ ኩንግ ይህን ሲናገሩ ብዙዎችን ግራ የሚያጋባ አንድ ችግር መጥቀሳቸው እንደ ነበር ልታስተውል ትችላለህ:- ሁሉን ቻይና አፍቃሪ የሆነው አምላክ ይህ ሁሉ ሥቃይና መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው? ሰዎች እንዲህ ዓይነቱን ጥያቄ ሲጠይቁ ሰምተህ አታውቅም? ማንኛውም የርኅራኄ ስሜት ያለው ሰው ኩንግ “የማያቋርጥ ደም መፋሰስ፣ ላብና እንባ፣ ሥቃይ፣ ሐዘንና ፍርሃት፣ ብቸኝነትና ሞት” ብለው በገለጹት ነገር ያዝናል። እንዲያውም በታሪክ ዘመናት ሁሉ በሚልዮን በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለ የመከራና የሰቆቃ መዓት ታይቷል ሊባል ይችላል።​— ኢዮብ 14:​1

“በመከራና በሐዘን” የተሞላ

በጦርነት ምክንያት የመጣውን ሥቃይና መከራ እስቲ አስበው! ሥቃዩ የሚደርሰው በቀጥታ የጉዳቱ ሰለባ በሆኑ ሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ልጆቻቸውና ሌሎች ሰዎች በጭካኔ በመገደላቸው ምክንያት ሐዘን ላይ በወደቁ ወላጆችና ዘመዶቻቸው ላይ ጭምር ነው። “ባለፉት 10 ዓመታት ብቻ በታጠቁ ኃይሎች መካከል በተነሡ ግጭቶች 1.5 ሚልዮን ሕፃናት ተገድለዋል” ሲል በቅርቡ ቀይ መስቀል ተናግሮ ነበር። በ1994 ሩዋንዳ ውስጥ “በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወንዶች፣ ሴቶችና ሕፃናት በአሠቃቂ ሁኔታ ሆን ተብሎ በዘዴ ተገድለዋል” ሲል ቀይ መስቀል ዘግቧል።

ከዚህም በተጨማሪ ሕፃናትን የሚያስነውሩ ሰዎች ያደረሱትን ሥቃይ መዘንጋት የለብንም። አንድ የልጆች ተንከባካቢ ካስነወረው በኋላ ልጅዋ ራሱን እንደገደለ የገለጸች አንዲት ሐዘንተኛ እናት “ልጄን ያስነወረው ግለሰብ . . . ልጄንም ሆነ ሌሎች በርካታ ወንዶች ልጆችን ማንም ሊገምተው ከሚችለው በላይ በዘዴና አስነዋሪ በሆነ መንገድ አበላሽቷቸዋል” ብላለች። በተጨማሪም “ሳይያዝና ምንም ሳይቀጣ 25 ዓመታት ሙሉ ሰዎችን አፍኖ ሲወስድ፣ አስገድዶ ሲደፍር፣ ሲያሠቃይና ሲገድል” ከኖረ በኋላ ብሪታንያ ውስጥ እንደተያዘው ዓይነት ርኅራኄ የሌላቸው ነፍሰ ገዳዮች ወይም ተከታታይ ግድያዎችን የፈጸሙ ወንጀለኞች የጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎች የሚደርስባቸውን ሰቆቃ አስብ። በታሪክ ዘመናት ሁሉ ሥቃይና መከራ በሚያመጣ መንገድ ወንዶችና ሴቶች አንዱ በሌላው ላይ ያደረሱት ጉዳት ገደብ ያለው አይመስልም።​— መክብብ 4:​1-3

ከዚህም ሌላ ስሜታዊና አካላዊ ሕመም የሚያስከትለውን ሥቃይና መከራ እንዲሁም አንድ የሚያፈቅሩት ሰው ያለ ዕድሜው ሲቀጭ ቤተሰቦቹ የሚሰማቸውን መሪር ሐዘን መጥቀስ ይቻላል። የረሃብ ወይም የሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎች ሰለባ የሆኑ ሰዎች የሚሰማቸው ስጋትም አለ። ሙሴ የ70 ወይም የ80 ዓመት ዕድሜያችን “በመከራና በሐዘን የተሞላ” ነው ሲል በገለጸው ሐሳብ ብዙዎች እንደሚስማሙ አያጠራጥርም።​— መዝሙር 90:​10 የ1980 ትርጉም

የአምላክ ዓላማ ነበርን?

አንዳንዶች እንደሚሉት ይህ የማያቋርጥ ሥቃይና መከራ የደረሰው ለመረዳት አስቸጋሪ በሆነው በአምላክ አሠራር ምክንያት ነውን? ‘በመጪው ዓለም’ ያለውን ሕይወት ሙሉ በሙሉ ለመረዳት አሁን የግድ መሠቃየት አለብን? ፈረንሳዊው ፈላስፋ ቴያር ደ ሻርደ “የሚገድለውና አካልን ለመበስበስ የሚዳርገው ሥቃይ ለፍጡሩ አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም በሕይወት እንዲኖርና መንፈስ እንዲሆን ያስችለዋል” ያለው እውነት ነውን? (የቴያር ደ ሻርደ ሃይማኖት፣ The Religion of Teilhard de Chardin; ጋደል አድርገን የጻፍነው እኛ ነን።) በፍጹም አይደለም!

አንድ አሳቢ የሆነ ንድፍ አውጪ ሆን ብሎ ለሕይወት አስጊ የሆነ አካባቢ ከፈጠረ በኋላ ይህ ሁኔታ ከሚያስከትላቸው ውጤቶች ሰዎችን ቢያድን ርኅራኄ አለኝ ሊል ይችላልን? በፍጹም አይችልም! አንድ አፍቃሪ አምላክ ለምን እንደዚህ ያደርጋል? ታዲያ አምላክ ሥቃይና መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው? ሥቃይና መከራ ይወገድ ይሆን? የሚቀጥለው ርዕስ እነዚህን ጥያቄዎች ያብራራል።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

WHO photo by P. Almasy

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ