የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w98 2/15 ገጽ 28-29
  • ምሥራቹን ለብዙ ሰዎች ማዳረስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ምሥራቹን ለብዙ ሰዎች ማዳረስ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምንድን ነው የምለው?
  • ያልተጠበቁና አርኪ የሆኑ ውጤቶች
  • መጽሔቶቻችንን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙባቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • የማያዳላውን አምላክ ይሖዋን ምሰሉት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • የሰዎችን ትኩረት የሚስቡ የተወሰኑ ርዕሶችን ምረጡ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • በማንኛውም ቦታ ምሥራቹን ስበኩ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
w98 2/15 ገጽ 28-29

ምሥራቹን ለብዙ ሰዎች ማዳረስ

በምኖርበት አገር ውስጥ ስለሚኖሩ ሰዎች ሳስብ አብዛኛዎቹ የይሖዋ ምሥክሮችን የሚያውቁት በዜና ከሚቀርቡት ዘገባዎች ብቻ እንደሆነ ተገነዘብኩ። እነዚህ ሰዎች ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ማንነትና ምን ብለው እንደሚያምኑ በትክክል ማወቅ እንዲችሉ ቀርቦ ማነጋገር ያስፈልጋል ብዬ አሰብኩ። ሆኖም መርዳት የምችለው እንዴት ነው? የጉባኤ ሽማግሌ የሆነው ባለቤቴ ጥበብ ያለበት መመሪያና ሐሳብ ሰጠኝ።

ጥር 8, 1995 በወጣው ንቁ! መጽሔት ላይ “ተግባራዊ ማጽናኛ የሚሰጡ መጽሔቶች” በሚል ርዕስ ከቀረበው ትምህርት ጥሩ ሐሳብ አገኘን። ጽሑፉ ስለ አንዲት ምሥክር የስብከት ሥራ ሲናገር እንዲህ ይላል:- “ሌሎች ምሥክሮች ዝም ብለው በቤታቸው ያከማቿቸው የቆዩ ንቁ! መጽሔቶች መሰብሰብን ሥራዬ ብላ ተያያዘችው። ከዚያም በአንዳንዶቹ ርዕሶች ላይ ጥሩ ፍላጎት ሊያሳዩ ይችላሉ ብላ ወዳሰበቻቸው መሥሪያ ቤቶች ትሄዳለች።”

በባለቤቴ አጋዥነት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ መጽሔቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰበሰብኩ። ከእነዚህ ውስጥ ቀርቤ ለማነጋግራቸው ሰዎች ተስማሚ የሆኑ የተለያዩ ርዕሶች ለመምረጥ ቻልኩ።

የስልክ ማውጫዎችንና አንዳንድ መረጃዎችን በመጠቀም የሆስፒታሎችን፣ ወጣቶች የሚኖሩባቸውን ሆስቴሎችና አረጋውያን የሚጦሩባቸውን ተቋማት አድራሻ የያዘ ዝርዝር አዘጋጀሁ። ከዚህም በተጨማሪ የቀብር ጉዳይ አስፈጻሚ ባለ ሥልጣናት፣ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና የተማሪ አማካሪዎች፣ የሬሳ መርማሪዎች እንዲሁም የወህኒ ቤትና የፍርድ ቤት አስተዳዳሪዎችን በዝርዝር መዘገብኩ። ዝርዝሩ ውስጥ የአልኮልና የዕፅ ሱሰኞች መርጃ ተቋማት፣ ስለ ተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም ክትትል የሚያደርጉ፣ የአካልና የጦር ጉዳተኞች እንዲሁም ስለ አመጋገብ ጥናት የሚያደርጉ ማኅበራት ዲሬክተሮችን አካተትኩ። የደኅንነት፣ የማኅበራዊ አገልግሎትና የቤተሰብ ጉዳዮችን የሚከታተሉ ቢሮዎች ሥራ አስኪያጆችንም አልዘነጋሁም።

ምንድን ነው የምለው?

ሰዎቹን ለማነጋገር በምሄድበት ጊዜ በመጀመሪያ የማደርገው ነገር ማንነቴን በግልጽ ማሳወቅ ነበር። ከዚያም የመጣሁበት ዓላማ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ እንደሚወስድ እገልጻለሁ።

ከኃላፊው ጋር ፊት ለፊት ከተገናኘሁ በኋላ እንደሚከተለው እላለሁ:- “እኔ የይሖዋ ምሥክር ነኝ። ሆኖም እዚህ የመጣሁት ሃይማኖታዊ ውይይት ለማድረግ አይደለም፤ በሥራ ሰዓት እንደዚህ ማድረግ ተገቢ ላይሆን ይችላል።” አብዛኛውን ጊዜ ሁኔታው ይበልጥ ዘና ያለ ይሆናል። ከዚያም የምናገረውን ከሁኔታው ጋር በማስማማት እንዲህ በማለት እቀጥላለሁ:- “የመጣሁት በሁለት ምክንያቶች የተነሳ ነው። በመጀመሪያ በእርሶ ቢሮ አማካኝነት እየተካሄደ ላለው ሥራ ያለኝን አድናቆት ለመግለጽ እፈልጋለሁ። ደግሞም እኮ አንድ ሰው በአጠቃላይ ለኅብረተሰቡ በማሰብ የሚያጠፋውን ጊዜና ጉልበት አቅልሎ መመልከት ተገቢ አይደለም። እናንተ የምታደርጉት ጥረት በእርግጥ የሚያስመሰግን ነው።” ይህ ዓይነቱ አቀራረብ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎችን ያስገርማቸዋል።

በዚህ ጊዜ ሰውዬው የመጣሁበት ሁለተኛው ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ይጓጓል። እንዲህ በማለት እቀጥላለሁ:- “የመጣሁበት ሁለተኛው ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታተመው የንቁ! መጽሔታችን እርስዎ ከሚሠሩት ዓይነት ሥራና ከሥራው ጋር ስለተያያዙ ችግሮች ትኩረት ሰጥተው የሚናገሩ አንዳንድ ርዕሶች ስላገኘሁ ነው። መቼም ዓለም አቀፋዊ ስርጭት ያለው መጽሔት ስለ እነዚህ ችግሮች ምን እንደሚናገር ለማወቅ እንደሚፈልጉ እርግጠኛ ነኝ። እነዚህን ቅጂዎች ብሰጥዎት ደስ ይለኛል።” አብዛኛውን ጊዜ ጥረቴን እንደሚያደንቁ ይነግሩኛል።

ያልተጠበቁና አርኪ የሆኑ ውጤቶች

ይህን አቀራረብ ስጠቀም አብዛኛዎቹ ወዳጃዊ በሆነ መንገድ ተቀብለውኛል። የማይቀበሉት ከ17 ሰዎች መካከል አንዱ ብቻ ቢሆን ነው። ያልተጠበቁና አርኪ የሆኑ በርካታ ተሞክሮዎች አጋጥመውኛል።

ለምሳሌ ያህል አንድ የአውራጃ ትምህርት ቤት ተቆጣጣሪን ለማግኘት የቻልኩት አራት ጊዜ ተመላልሼ ከሞከርኩና በትዕግሥት ከተጠባበቅሁ በኋላ ነበር። በጣም ሥራ የሚበዛበት ሰው ነበር። ሆኖም ወዳጃዊ በሆነ መንፈስ የተቀበለኝ ከመሆኑም በላይ ለተወሰነ ጊዜ አነጋግሮኛል። ለመሄድ ስነሳ “ጥረትሽን ከልብ አደንቃለሁ፤ እንዲሁም የሰጠሽኝን ጽሑፎች በደንብ አድርጌ አነባቸዋለሁ” አለኝ።

በሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ አንድ የአውራጃው ፍርድ ቤት ስሄድ በመካከለኛ እድሜ ላይ የሚገኘውን የፍርድ ቤቱን ዋና ዳኛ አገኘሁት። ቢሮው በገባሁ ጊዜ የሚያነበውን ነገር አቋርጦ በቁጣ ቀና ብሎ ተመለከተኝ።

“የሥራ ሰዓት ማክሰኞ ጠዋት ብቻ ነው፤ በዚያን ቀን ማንኛውንም መረጃ ለመስጠት እገኛለሁ” በማለት ቆጣ ብሎ መለሰልኝ።

“ተገቢ ባልሆነ ሰዓት በመምጣቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ” ብዬ ከመለስኩ በኋላ ቀጠል አድርጌ “በሌላ ጊዜ ተመልሼ ብመጣ ደስ ይለኛል። ሆኖም የመጣሁት ለሥራ ጉዳይ አልነበረም” አልኩ።

በዚህ ጊዜ ዳኛው የመጣሁበትን ጉዳይ ለማወቅ ጉጉት አደረበት። ረገብ ባለ ድምፅ ምን እንደምፈልግ ጠየቀኝ። ማክሰኞ ዕለት ተመልሼ እንደምመጣ ደግሜ ተናገርኩ።

ከጠበቅሁት ውጪ “እባክሽ ተቀመጭ” ብሎ ግድ አለኝ። “የምትፈልጊው ምንድን ነው?”

ጥሩ የሆነ ወዳጃዊ ጭውውት አደረግን እንዲሁም በጣም ሥራ በዝቶበት ስለነበር መጀመሪያ ላይ ወዳጃዊ ባልሆነ መንገድ ስለመለሰልኝ ይቅርታ ጠየቀኝ።

ከዚያም “የይሖዋ ምሥክሮች ደስ የሚሉኝ ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?” ብሎ ጠየቀኝ። “የሚመሩባቸው ጠንካራ የሆኑ መሠረታዊ ሥርዓቶች አሏቸው፣ ከዚያ ፍንክች አይሉም። ሂትለር የተቻለውን ሁሉ አድርጓል ሆኖም ምሥክሮቹ ወደ ጦርነት አልዘመቱም።”

ሁለታችንም ወደ አንድ ቢሮ በገባን ጊዜ እዚያ የነበሩት ጸሐፊዎች አስታወሱን። ከዚያም ዋና ጸሐፊዋ “ፕሬዚዳንቱ ማንንም ተቀብሎ አነጋግሮ አያውቅም” አለችን።

“እኛ ግን የይሖዋ ምሥክሮች ስለሆንን እንድንገባ ይፈቅድልናል” ብዬ በእርጋታ መለስኩላት። “የመጣነው አቤቱታ ለማቅረብ አይደለም፤ በዚያ ላይ ደግሞ የመጣንበት ዓላማ ከሦስት ደቂቃ በላይ አይፈጅም።” በውስጤ “እባክህ ይሖዋ ይህ ጥሩ አጋጣሚ እንዲሆንልን እርዳን!” ብዬ ከልብ ጸለይኩኝ።

ጸሐፊዋም በምንቸገረኝ ዓይነት “እሺ እግዲያው እሞክራለሁ” ብላን ሄደች። ከአንድ ከሁለት ደቂቃ ገደማ በኋላ (ለእኔ ዓመት ነው የመሰለኝ) ፕሬዚዳንቱን አስከትላ ተመልሳ መጣች። ምንም ነገር ሳይናገር ሁለት በሮች አልፈን ወደ ቢሮው እየመራ ወሰደን።

ውይይታችንን እየቀጠልን ስንሄድ ሰውዬው ይበልጥ ተግባቢ እየሆነ መጣ። የንቁ! መጽሔት ልዩ እትሞችን ባበረከትንለት ጊዜ በፈቃደኝነት ተቀበለን። ስለ ሥራችን ዓላማ ጥሩ ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችለንን ይህን አጋጣሚ በማግኘታችን ይሖዋን አመሰገንን።

ያጋጠሙኝን በርካታ አስደሳች ተሞክሮዎች መለስ ብዬ ሳስታውስ ሐዋርያው ጴጥሮስ “እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ” ሲል የተናገረውን ይበልጥ መገንዘብ ችያለሁ። (ሥራ 10:​34, 35) የአምላክ ፈቃድ የተለያየ ዓይነት አስተዳደግ፣ ቋንቋና የኑሮ ደረጃ ያላቸው ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሰው ልጆችና ለምድር ያለውን ዓላማ የማወቅ አጋጣሚ እንዲያገኙ ነው።​—⁠ተጽፎ የተላከልን

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ