የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 7/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ጥሩ ምግባር ክፋትን ድል የሚያደርግበት ቀን ይመጣ ይሆን?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 7/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ክፋት ከየት መጣ?

ዲያብሎስ የዓለምን መንግሥታት በሙሉ ለኢየሱስ ለመስጠት ግብዣ ቢያቀርብለትም ኢየሱስ ግን አልተቀበለም

ኢየሱስን መጥፎ ነገር እንዲሠራ ሊያባብለው የሞከረው ማን ነው?—ማቴዎስ 4:8-10

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሰላማዊ፣ ሐቀኛና ደግ መሆን ይፈልጋሉ። ታዲያ ዓመፅ፣ ግፍና ጭካኔ የበዛው ለምንድን ነው? ዘግናኝ የዜና ዘገባዎች የተለመዱ ነገሮች እየሆኑ መጥተዋል። ሰዎች መጥፎ ነገር እንዲያደርጉ የሚገፋፋቸው አካል ይኖር ይሆን?—1 ዮሐንስ 5:19⁠ን አንብብ።

አምላክ ሰዎችን የፈጠራቸው መጥፎ ነገር የመሥራት ዝንባሌ እንዲኖራቸው አድርጎ ነው? በፍጹም፤ ይሖዋ አምላክ ሰዎችን የፈጠራቸው በራሱ መልክ ይኸውም የእሱን ፍቅር የማንጸባረቅ ዝንባሌ እንዲኖራቸው አድርጎ ነው። (ዘፍጥረት 1:27፤ ኢዮብ 34:10) ይሁን እንጂ አምላክ ለሰዎች የመምረጥ ነፃነት በመስጠትም አክብሯቸዋል። የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን መጥፎ ነገር ለማድረግ በመረጡ ጊዜ የአምላክን ምሳሌነት ለመከተል እምቢተኛ በመሆናቸው ፍጽምና የጎደላቸው ሆኑ። እኛም ከእነሱ ኃጢአት የመሥራት ዝንባሌን ወርሰናል።—ዘዳግም 32:4, 5⁠ን አንብብ።

ክፋት ምንጊዜም በውስጣችን ይኖራል?

አምላክ መጥፎ ዝንባሌዎቻችንን እንድንቆጣጠር ይፈልግብናል። (ምሳሌ 27:11) በመሆኑም ስህተት የሆነውን ነገር ከመፈጸም መቆጠብና እውነተኛ ደስታ ማግኘት የምንችልበትን መንገድ ያስተምረናል። ይሁንና በአሁኑ ጊዜ የአምላክን ፍቅር ፍጹም በሆነ መንገድ መኮረጅ አንችልም።—መዝሙር 32:8⁠ን አንብብ።

በአሁኑ ጊዜ ክፋት ተንሰራፍቶ የሚገኝ ቢሆንም አምላክ ሁሉም ሰው የክፋትን አሳዛኝ መዘዞች ማየት እንዲችል ክፋት እንዲኖር የፈቀደው ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው። (2 ጴጥሮስ 3:7-9) በቅርቡ ግን ምድር አምላክን በሚታዘዙ ደስተኛ ሰዎች ትሞላለች።—መዝሙር 37:9-11⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ