የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 4/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሰው ልጆች ወደፊት ምን ይጠብቃቸዋል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ኢየሱስ ወደፊት ምን ያደርጋል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 4/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የሰው ልጆች ወደፊት ምን ይጠብቃቸዋል?

አንድ ቤተሰብ ከእነሱ የተለየ ዘር ላላት አረጋዊት ሴት አሳቢነታቸውን ሲገልጹ

ኢየሱስ መሞቱ፣ ሰዎች እርስ በርሳቸው የሚተሳሰቡበት ማኅበረሰብ እንዲኖር መንገድ የከፈተው እንዴት ነው?

የሰው ልጆች በሳይንስ መስክ እድገት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ጥያቄ የለውም። ይሁንና እርስ በርስ ከልብ የሚተሳሰቡ ሰዎች ያሉበት ማኅበረሰብ እንዲኖር ማድረግ ይችሉ ይሆን? በፍጹም። በዛሬው ጊዜ በዓለም ላይ ራስ ወዳድነትና ስግብግብነት ነግሷል። ሆኖም የአምላክ ዓላማ የሰው ዘር የተሻለ ሕይወት እንዲኖረው ነው።—2 ጴጥሮስ 3:13⁠ን አንብብ።

ወደፊት፣ እርስ በርስ የሚዋደዱ ሰዎች ያሉበት ዓለም አቀፋዊ ማኅበረሰብ እንደሚኖር የአምላክ ቃል ይናገራል። ሰዎች ያለ ስጋት የሚኖሩ ሲሆን ጉዳት የሚያደርስባቸውም አይኖርም።—ሚክያስ 4:3, 4⁠ን አንብብ።

ራስ ወዳድነት የሚወገደው እንዴት ነው?

የሰው ልጅ መጀመሪያ ሲፈጠር የራስ ወዳድነት ዝንባሌ ፈጽሞ አልነበረውም። ይሁንና የመጀመሪያው ሰው፣ አምላክን ባለመታዘዙ ፍጽምናውን አጣ። እኛም የራስ ወዳድነት ዝንባሌን ከእሱ ወረስን። ያም ቢሆን አምላክ በኢየሱስ አማካኝነት የሰው ልጆች ወደ ፍጽምና ደረጃ እንዲደርሱ ያደርጋል።—ሮም 7:21, 24, 25⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ መሥዋዕት ሆኖ በመሞት የመጀመሪያው ሰው ዓመፅ ያስከተለውን ውጤት አስወግዷል። (ሮም 5:19) በመሆኑም ኢየሱስ፣ ሰዎች መጥፎ ነገር እንዲያደርጉ ከሚገፋፋ የራስ ወዳድነት ዝንባሌ ነፃ የመሆን ግሩም ተስፋ እንዲኖራቸው አድርጓል።—መዝሙር 37:9-11⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 5 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ