የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp19 ቁጥር 2 ገጽ 3
  • ሕይወት ከባድ ሲሆንብህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሕይወት ከባድ ሲሆንብህ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሕይወት መራራ ሲሆን
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • የምትወደው ሰው ሲሞት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • መከራ ሲደርስ
    ንቁ!—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
wp19 ቁጥር 2 ገጽ 3
አንዲት ወጣት በሥራ ቦታዋ ሆና ስታለቅስ

ሕይወት ከባድ ሲሆንብህ

ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ በሆነበት ወቅት ሕይወት አስደሳች ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ሕይወት ከባድ እንዲሆንብህ የሚያደርጉ አንዳንድ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙህስ?

ለምሳሌ ያህል፣ በከባድ አውሎ ነፋስ ምክንያት አብዛኛውን ንብረቷን ያጣች በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር ሳሊa የተባለች ሴት እንዲህ ብላለች፦ “የሚሰማኝ ጭንቀት ልሸከመው ከምችለው በላይ እንደሆነ ተሰምቶኝ ነበር። ‘አሁንስ በቅቶኛል’ ያልኩባቸው ብዙ ጊዜያት ነበሩ።”

በሕይወታችን ውስጥ ሊያጋጥመን የሚችለው ሌላው ተፈታታኝ ሁኔታ ደግሞ የምንወደውን ሰው በሞት ማጣት ነው። በአውስትራሊያ የምትኖረው ጃኒስ እንዲህ ብላለች፦ “ሁለቱንም ወንዶች ልጆቼን ሞት ሲነጥቀኝ ሁሉ ነገር ጨለመብኝ፤ ወደ ቀድሞ ሕይወቴ ለመመለስ ብዙ ጥረት ጠይቆብኛል። ‘ከዚህ በላይ መሸከም አልችልም! እባክህ ሞቼ ልገላገል። ዳግመኛ መንቃት አልፈልግም’ በማለት አምላክን ተማጽኜው ነበር።”

በሌላ በኩል ደግሞ ዳንኤል፣ ባለቤቱ በትዳራቸው ላይ ክህደት እንደፈጸመች ሲያውቅ ስሜቱ ክፉኛ ተጎድቶ ነበር። እንዲህ ብሏል፦ “ባለቤቴ ምንዝር እንደፈጸመች ስትነግረኝ ልቤ ላይ ጩቤ የተሰካብኝ ያህል ሕመም ተሰምቶኝ ነበር። ይህ አካላዊ ሕመም በተደጋጋሚ እየመጣ ለብዙ ወራት አሠቃይቶኛል።”

ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም በሚከተሉት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሥር እንኳ፣ ‘በሕይወት መኖር ዋጋ አለው’ የምንልበትን ምክንያት ያብራራል፦

  • የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም

  • የምትወደው ሰው ሲሞት

  • የትዳር ጓደኛ ክህደት ሲፈጽም

  • ከከባድ ሕመም ጋር ስትታገል

  • በሕይወት መኖር ሲያስጠላህ

በመጀመሪያ፣ የተፈጥሮ አደጋ በሚያጋጥምበት ጊዜ ሁኔታውን መቋቋም የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመልከት።

a በእነዚህ ተከታታይ ርዕሶች ውስጥ የተጠቀሱት አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ