“እሱ ስለ እናንተ ያስባል”
በሕይወትህ ውስጥ አንዳንድ የምታምናቸው ሰዎች እንዳሰብከው ሆነው ባይገኙ እንኳ ፈጽሞ የማያሳፍርህ አንድ አካል አለ። ይህ አካል ማን ነው?
በጥንት ዘመን የኖረው ንጉሥ ዳዊት “የገዛ አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳ ይሖዋ ራሱ ይቀበለኛል” ብሏል።—መዝሙር 27:10
“የምሕረት አባትና የመጽናናት ሁሉ አምላክ” የሆነው ይሖዋ “በሚደርስብን መከራ ሁሉ ያጽናናናል።”—2 ቆሮንቶስ 1:3, 4
“የሚያስጨንቃችሁን . . . ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ፤ ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል።”—1 ጴጥሮስ 5:7
አምላክ ለአንተ ያለውን አሳቢነት ያሳየው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 08 ተመልከት። መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል።