የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/93 ገጽ 8
  • እውነተኛ መመሪያ የሚሰጥ መጽሐፍ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እውነተኛ መመሪያ የሚሰጥ መጽሐፍ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ—አምላክ ለሰው ሁሉ መመሪያ እንዲሆን የሰጠው መጽሐፍ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ሌሎች አንድን ታላቅ ሀብት እንዲያውቁ መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • የአምላክ ቃል መመሪያ ይሰጣል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ከእውነተኛው አምላክ የሚገኘው እውቀት ወደ ሕይወት ይመራል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
km 11/93 ገጽ 8

እውነተኛ መመሪያ የሚሰጥ መጽሐፍ

1 ባለፈው መቶ ዘመን ዓለም በከፍተኛ ሁኔታ ተለውጣለች። በመገናኛ፣ በመድኃኒትና በመጓጓዣ በኩል እድገት ቢኖርም የቤተሰብ ኑሮ ግን እያሽቆለቆለ ነው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ያለማቋረጥ በሚለዋወጠው የሰው ፍልስፍና ይመራሉ።

2 በፍጥነት በሚለዋወጠው በዚህ ዓለም የይሖዋ ሕዝቦች ቃሉን አጥብቀው በመከተላቸው ብዙ ጥቅም አግኝተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ በሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት ሳይለወጥ ቆይቷል፤ ምክሮቹም ዛሬ ያሉትን ችግሮች ለመቋቋም በተግባራዊነታቸው ተወዳዳሪ የሌላቸው ናቸው። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ዘመናዊ ለሆነው ለጊዜያችን የሚሆን እውነተኛ መመሪያ እንደሚሰጥ እንዲገነዘቡ እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን?

3 “ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት” የተባለውን ትራክት ትተህለት ከነበረ ተመልሰህ ስትሄድ እንዲህ ልትል ትችላለህ፦

◼ “መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ መልእክት መሆኑን በግልጽ ስለሚናገርና አምላክ ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የዘላለም ሕይወት እንድናገኝ የጋበዘን መሆኑን የሚናገር በመሆኑ ስለነዚህ ተስፋዎች ይበልጥ ለማወቅ መጽሐፉን መመርመሩ ጠቃሚ ሆኖ አይሰማዎትም? [ሐሳብ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ ስለመጪው አዲስ ዓለም የሚናገረውን ትንቢት ልብ ይበሉ።” [በትራክቱ ውስጥ በገጽ 3 ላይ ካለው “በአምላክ አዲስ ዓለም ውስጥ የሚኖረው ሕይወት” ከሚለው ንዑስ ርዕስ ላይ ያለውን ሐሳብ አንብብና ተወያዩበት።] በትራክቱ ውስጥ በገጽ 5 ላይ ወይም መጽሐፍ ቅዱስ ለሰው ልጆች የያዘውን አስደናቂ ተስፋ ይበልጥ ጎላ አድርጎ የሚገልጸውን መጽሐፍ ቅዱስ — የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? በተባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ በገጽ 161 ላይ ያለውን ሐሳብ አወያየውና ለሌላ ጉብኝት የሚሆን መሠረት ጣል።

4 ሰውየው “መጽሐፍ ቅዱስ — የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?” የተባለው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ተበርክቶለት ከነበረና መጽሐፍ ቅዱስ ያለው ተግባራዊ ጥቅም ፍላጎት አሳድሮበት በምዕራፍ 12 ላይ ያሉትን የተወሰኑ መሠረታዊ ሥርዓቶች ጠቅሰህለት ከነበረ እንዲህ ልትለው ትችላለህ፦

◼ “ለዘመናችን ተገቢ የሆነ ነገር ብናገኝ ደስ ይለናል፤ አይደለም እንዴ? ረብሻንና ጦርነትን ማስቆም ለዘመናችን የሚገባ ነገር ነው ቢባል አይስማሙምን? [ሐሳብ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ሰዎች ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በሰላም አብሮ መኖርን ቢማሩ እነዚህን ችግሮች ለማጥፋት የሚያስችል ጥሩ ጅምር ይሆን ነበር፤ አይደለም? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ ይህ እንደሚሆን አስቀድሞ ተናግሯል።” [ኢሳይያስ 2:2, 3⁠ን አንብብለት።] ይህ የሚፈጸመው በአምላክ መንግሥት አማካኝነት መሆኑን ለማሳየት ምክንያቱን ማስረዳት በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 228–30 ላይ ባሉት ተጨማሪ ሐሳቦች ልትጠቀም ትችላለህ። ከዚያ እንዲህ ብለህ ጠይቀው:- “ይህ መቼ ይመጣ ይሆን ብለው አስበው ያውቃሉ?” ሰውየው በሚመቸው ሰዓት ተመልሰህ መጥተህ በዚህ ጥያቄ ላይ ለመወያየት ፈቃደኛ መሆንህን ግለጽለት።

5 “አዲሲቱ ዓለም ትርጉም” አበርክተህለት ከነበረ ተመልሰህ ስትሄድ እንዲህ ልትለው ትችላለህ፦

◼ “ያበረከትኩልዎትን መጽሐፍ ቅዱስ ሲያነቡ መጽሐፍ ቅዱሱ ከዳር እስከ ዳር በአምላክ የግል ስም እንደሚጠቀም ሳያስተውሉ አልቀሩም። ይህ ከብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይልቅ የተደረገ ትልቅ መሻሻል ነው። ምንም እንኳን አንዳንድ ሰዎች ይሖዋ በሚለው ስም ለመጠቀም ቢያቅማሙም አምላክ ስሙን የገለጠልን ከረጅም ጊዜ በፊት መሆኑንና አገልጋዮቹም እርሱ እውነተኛና ሕያው አምላክ መሆኑን ለይተው እንዲያውቁት በስሙ እንዲጠቀሙ እንዳበረታታቸው መዘንጋት የለብንም። መዝሙራዊው በመዝሙር 83:18 ላይ የጻፈውን ይመልከቱ።” ጥቅሱን አንብብና ሰውየው ሐሳብ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ባሳየው ፍላጎት ላይ በመመርኮዝ ምክንያቱን ማስረዳት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 191 ላይ ባለው “ይሖዋ” በሚለው ርዕስ ሥር የሚገኘውን ሐሳብ መጠቀም ትችላለህ።

6 ሰው የሚያስፈልገውን መመሪያ የሚሰጠው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። (ኤር. 10:23) ስለ አምላክ ዓላማዎች ለመማርና በርሱ ፊት ሞገስ ለማግኘት የምንችልበት ብቸኛው መንገድ የአምላክን ቃል ማጥናት ብቻ ነው። እንግዲያው ሌሎች ሰዎች ጥበብ ካለበትና ሊሠራ ከሚችለው ምክሩ እንዲጠቀሙ አጥብቀን እንጋብዛቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ