እውነትን ለሌሎች ለማካፈል በመጽሔቶች ተጠቀም
1 በተጋነኑ ማስታወቂያዎች፣ በአሳሳች የፖለቲካ ተስፋዎችና በዓለም አቀፍ ደረጃ ይህን አድርገናል ወይም ሠርተናል እየተባለ በሚነገረው ልፈፋ ምክንያት ዛሬ ባለው ኅብረተሰብ ዘንድ እውነትን ለያዘና በሐቅ ላይ ለተመሠረተ እውቀት ሰዎች የነበራቸው ግምት እየመነመነ መጥቷል። የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች ስለ አምላክ መንግሥት እውነቱን የሚያስታውቁና የአምላክ መንግሥት በሚያመጣው ዘላለማዊ በረከት ለመደሰት ሁሉም ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያስረዱ እነርሱ ብቻ ስለሆኑ ልዩ መጽሔቶች ናቸው።
2 በአንድ አገር ውስጥ በማስታወቂያ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ባለ ሥልጣን የሆነና የእነዚህን ሁለት መጽሔቶች ዋጋማነት የተገነዘበ አንድ ሰው መጽሔቶቹ እንዲሰራጩ ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ ሆኗል። እንዲህ አለ:- “ተወዳዳሪ የላቸውም ከሚባሉት መጽሔቶች መካከል አንዱ መጠበቂያ ግንብ እንደሆነ ይሰማኛል። መጽሔቶቹ እንዲሰራጩ ለመርዳት በጣም ደስተኛ ነኝ።” የዘላለም ሕይወት የሚያሰጥ እውቀት የያዙትን እነዚህን መጽሔቶች በማሰራጨት ሌሎችን መርዳቱ መብታችን ነው። (ዮሐ. 17:3) በግንቦት ወር እነዚህን ጠቃሚ መጽሔቶች ማበርከት የምትችለው እንዴት ነው? ቀጥሎ የቀረቡትን ሐሳቦች ጠቃሚ ሆነው ታገኛቸው ይሆናል።
3 የሚያዝያ 15 “መጠበቂያ ግንብ” ን የምታበረክት ከሆነ እንዲህ ልትል ትችላለህ፦
◼ “በዓለም ካሉት መጻሕፍት ሁሉ በብዙ ቅጂዎች ስለተሸጠው መጽሐፍ ከሰዎች ጋር እየተነጋገርን ነው። የትኛው መጽሐፍ እንደሆነ ያውቁታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] እየተናገርን ያለነው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይህን ያህል ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን የገዙበት ጥሩ ምክንያት መኖር አለበት። ምክንያቱ በ2 ጢሞቴዎስ 3:16 ላይ ተገልጿል።” ጥቅሱን ካነበብክ በኋላ “እምነት የሚጣልበት አመራር ከየት ልታገኝ ትችላለህ?” በሚለው ርዕስ ሥር በገጽ 6, 7 ላይ የሚገኙትን ተስማሚ ነጥቦች አጉላለት። ከዚያም ኮንትራት እንዲገባ ጠይቀው። መጽሔቶቹ በተከታታይ እንዲደርሱት ኮንትራት እንዲገባ የቀረበለትን ሐሳብ ካልተቀበለ ሁለት መጽሔቶችንና አንድ ብሮሹር በመደበኛው ዋጋ ልታበረክትለት ትችላለህ።
4 ወይም የሚያዝያ 1ን እትም ስታበረክት አጠር ያለ መግቢያ ከተጠቀምክ በኋላ እንዲህ ልትል ትችላለህ፦
◼ “ሰዎች በዚህ የመጠበቂያ ግንብ እትም በገጽ 7 ላይ እንዳለው ባለ ሁኔታ መኖር ይችላሉ ብለው ያስባሉን? (ሰውዬው መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።) ከዚያም በገጽ 7 ላይ ባለው ሥዕል እንዲያተኩር አድርገውና ከሥዕሉ ሥር ያለውን መግለጫ አንብብለት። በዚያው ገጽ ላይ በአንቀጽ 1 ላይ በተጠቀሱት ጥቅሶች ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹ በቋሚነት እቤቱ ድረስ ቢላኩለት የሚያገኘውን ጥቅም ጎላ አድርገህ ግለጽለትና ኮንትራት እንዲገባ ጠይቀው።
5 በመጀመሪያ ላይ መጠነኛ ፍላጎት ያሳዩ ሆነው ምንም ውጤት ያላገኘህባቸው ሰዎች ስም ዝርዝር በተመላልሶ መጠየቅ መመዝገቢያህ ላይ ይኖር ይሆናል። ያሳዩት ፍላጎት መጠነኛ በመሆኑ ብቻ እየተመላለሱ መጠየቁ አስፈላጊ እንደሆነ አልተሰማህ ኖሮ ይሆናል። ይሁን እንጂ በዚህ መዝገብ ተጠቅመህ የመጽሔት ደንበኞች እንዲኖሩህ ልትሞክር ትችላለህ። አንድ ርዕስ በተለይ አንድን ሰው የሚስበው ሆኖ ከተሰማህ ያንን ግለሰብ ተመልሰህ መጠየቅና ርዕሱ ያለበትን መጽሔት ለማበርከት ግብ አድርግ።
6 መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት፦ ይህ የምሥክርነት መስጫ መንገድ ሰዎች ለመጽሔቶቹ ፍላጎት እንዲያሳድሩ የሚረዳ በጣም ጥሩ መንገድ ነው። ለዓይን ማራኪ ሆነው እንዲታዩ በጥንቃቄ የተዘጋጁት የመጽሔቶቹ ሽፋኖች ብቻቸውን ውይይት ለመጀመር በቂ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዲት እኅት የሥራ ባልደረቦቿ ሲያልፉ ማየት በሚችሉበት መንገድ ጠረጴዛዋ ላይ መጽሔቶቹን አስቀመጠች። ብዙ መጽሔቶችን ማበርከት ቻለች። በዚህ ወር ወደ ገበያ ስትሄዱ፣ ወደ ትምህርት ቤት ስትሄዱ፣ በአውቶቡስ ስትጓዙ ወይም በማንኛውም ቦታ ከሰዎች ጋር ስትገናኙ ማበርከት እንድትችሉ ጥቂት ቅጂዎችን ይዛችሁ ለመሄድ ግብ አድርጉ።
7 በመጠበቂያ ግንብ እና በንቁ! መጽሔቶች እየታገዝን ስለ ይሖዋና ስለእርሱ አምልኮ እጅግ አስፈላጊ ለሆኑ ጥያቄዎች መልስ አግኝተናል። በሚቻለው መንገድ ሁሉ ሌሎች “የእውነት አምላክ” የሆነውን ይሖዋን እንዲያውቁ ለመርዳት በእነዚህ መጽሔቶች ለመጠቀም እንፈልጋለን — መዝ. 31:5