በአገልግሎታችሁ ላይ መጽሔቶችን አበርክቱ
1, 2. መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች የሰዎችን ሕይወት ሊለውጡ የቻሉት እንዴት ነው?
1 “ማራኪ፣ ወቅታዊና የሚያነቃቁ።” “እስከ ዛሬ ካነበብኳቸው ሁሉ ይበልጥ የሚያበረታቱ መጽሔቶች።” እነዚህ አስተያየቶች በዓለም ዙሪያ የሚገኙ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን የሚያነቡ ሰዎች ያላቸውን አመለካከት በደንብ አድርገው ይገልጻሉ። በእርግጥም መጽሔቶቻችን “ሰዎች ሁሉ” ምሥራቹ እንዲደርሳቸው ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።—1 ጢሞ. 2:4
2 በንግድ ሥራ የተሰማራ አንድ ሰው ርዕሱ የማረከውን አንድ ንቁ! መጽሔት ወሰደ። በመቀጠልም መጠበቂያ ግንብ ያነበበ ሲሆን ይህም ዕድሜውን ሙሉ ሲያምንበት የነበረውን የሥላሴ ትምህርት እንዲመረምር አነሳሳው። ያደረገው ምርምር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያጠና የገፋፋው ሲሆን ከስድስት ወራት በኋላ ተጠመቀ። አንድ ሌላ ሰው ደግሞ መጽሔቶቹን ሁልጊዜ የሚቀበል ቢሆንም አያነባቸውም ነበር። የዚህ ሰው ሚስት ምሥክሮቹን ማግኘት የማትፈልግ ቢሆንም ባሏ የሚያመጣቸውን መጽሔቶች ግን ታነብ ነበር። ምድር ገነት ሆና በጻድቅ ሰዎች እንደምትሞላ የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ልቧን ነካት። ከጊዜ በኋላ እርሷ፣ ወንድ ልጇና ታናሽ እህቷ የይሖዋ አገልጋዮች ለመሆን ችለዋል።
3. ሁለቱንም መጽሔቶች በአንድ ላይ ማበርከታችን ምን ጥቅም አለው?
3 ሁለቱንም አንድ ላይ አበርክቱላቸው:- ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ምሳሌዎች እንደሚያሳዩት መጽሔቶቹን ማን እንደሚያነባቸው ወይም የትኛው ርዕስ የሰዎቹን ትኩረት እንደሚስብ ልናውቅ አንችልም። (መክ. 11:6) እንግዲያው በመግቢያችን ላይ የምንጠቀመው አንድ መጽሔት ብቻ ቢሆንም ንቁ! እና መጠበቂያ ግንብን አንድ ላይ አድርገን ማበርከታችን ጠቃሚ ነው። ለምናነጋግራቸው ሰዎች በርከት ያሉ የተለያዩ እትሞችን በአንድ ጊዜ ማበርከቱ ተገቢ የሚሆንባቸው ጊዜያትም አሉ።
4. መጽሔት ለማበርከት እንዴት ፕሮግራም ማውጣት እንችላለን?
4 በየሳምንቱ አንድ ቀን መጽሔት ለማበርከት ፕሮግራም ማውጣት ጠቃሚ ነው። በ2005 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ ላይ ሁሉም ቅዳሜዎች “የመጽሔት ቀን” ተብሎባቸዋል። የእያንዳንዱ ሰው ፕሮግራምና የአካባቢው ሁኔታ ሊለያይ ስለሚችል አንዳንዶች መጽሔቶችን ለማበርከት ሌላ ቀን ይመርጡ ይሆናል። አንተስ በሳምንቱ ውስጥ መጽሔት የምታበረክትበት ፕሮግራም አለህ?
5. መጽሔቶችን ለማበርከት የትኞቹን አጋጣሚዎች መጠቀም እንችላለን? ይህን ለማድረግስ ምን ሊረዳን ይችላል?
5 ግብ አውጡ:- በየወሩ ምን ያህል መጽሔት እንደምናበረክት ግብ ማውጣታችን መጽሔቶችን ለማበርከት የተለየ ትኩረት እንድንሰጥ ያደርገናል። የመጽሔት ደንበኛ አለህ? በአገልግሎት ለምታገኛቸው ሰዎች መጽሔቶችን ታበረክትላቸዋለህ? ከመንገድ ወደ መንገድ፣ በንግድ አካባቢዎችና ሕዝብ በብዛት በሚገኝባቸው ቦታዎች መጽሔቶችን ማበርከት ትችላለህ? በምትጓዝበት ጊዜ እንዲሁም ወደ ገበያ፣ ሆስፒታል ወይም ሌሎች ቦታዎች ስትሄድ መጽሔቶችን ትይዛለህ? ሌሎች ከመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለመርዳት የሚያስችልህ ማንኛውም አጋጣሚ እንዲያመልጥህ አትፍቀድ።
6. የቆዩ መጽሔቶችን እንዴት በጥሩ ሁኔታ ልንጠቀምባቸው እንችላለን?
6 በእጃችን ያሉ የቆዩ መጽሔቶችን ለማበርከትም ግብ ልናወጣ እንችላለን። መጽሔቶቹ ሳይበረከቱ ለአንድ ወይም ለሁለት ወራት ቢቆዩም ውስጡ ያለው እውቀት አሁንም ቢሆን ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። ፍላጎት ያላቸው ሰዎች መጽሔቶቹ እንዲደርሷቸው አድርጉ። መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ‘ባግባቡ እንደተነገረ ቃል’ ሆነውላቸዋል። (ምሳሌ 25:11) እነዚህን መጽሔቶች በመጠቀም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይሖዋን ለማወቅና ለማገልገል እንዲችሉ እንርዳቸው።