የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/98 ገጽ 8
  • መጽሔቶች መንግሥቱን ያስታውቃሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሔቶች መንግሥቱን ያስታውቃሉ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሔቶቻችንን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙባቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • በአገልግሎታችሁ ላይ መጽሔቶችን አበርክቱ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • መጽሔት ለማበርከት ጊዜ መድብ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • በመጠበቂያ ግንብ እና በንቁ! መጽሔቶች በጥሩ ሁኔታ መጠቀም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 4/98 ገጽ 8

መጽሔቶች መንግሥቱን ያስታውቃሉ

1 እኛ የይሖዋ ምሥክሮች ስለ አምላክ መንግሥት በቅንዓት በመስበክ ረገድ በሚገባ የታወቅን ነን። የምናሰራጫቸው መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ስለ አምላክ ዓላማ እንዲያውቁ በመርዳት ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። የሰው ልጆች ብቸኛ ተስፋ በሰማይ የሚገኘው የአምላክ መንግሥት እንደሆነ ስለሚገልጹ በእርግጥም የያዙት መልእክት ምስራች ነው።

2 መጽሔቶቹ የሰው ልጆች መሠረታዊ ፍላጎቶች በሆኑት ነገሮች ላይ ማለትም በስሜታዊ፣ በማኅበራዊና በመንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። በዓለም ዙሪያ የሥነ ምግባር ንጽሕናና የቤተሰብ እሴቶች ወደ አዘቅት እየወረዱ ስለሆነ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች እንዴት በሥራ ላይ ማዋል እንደሚቻል በማሳየት ሰዎች አኗኗራቸውን እንዲያሻሽሉ ይረዳሉ። በሚያዝያና ግንቦት ወር እነዚህን መጽሔቶች በማበርከት ደስታ እናገኛለን።

3 በእርግጥም ማራኪዎች ናቸው፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! በዓለም ዙሪያ በሚነገሩ በአብዛኞቹ ቋንቋዎች ይገኛሉ ለማለት ይቻላል። ይህም በመሆኑ መጽሔቶቻችን የታወቁ ናቸው። እነዚህ መጽሔቶች ሰዎችን የሚማርኩት ለምን እንደሆነ አንዳንድ ምክንያቶችን እንመልከት:-

◼ ትክክል ለሆነ ነገርና ለእውነት የቆሙ መጽሔቶች እንደመሆናቸው መጠን ጥሩና መጥፎ በሆኑ ነገሮች መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ ያስቀምጣሉ።

◼ አምላክ ምድርን በመንግሥታዊ አገዛዜ ሥር አደርጋለሁ ብሎ በገባው ቃል መሠረት ጽድቅ የሰፈነበት ገነት እንደሚመጣ ተስፋ ይሰጣሉ።

◼ የተለያየ አስተዳደግና ባህል ያላቸውን ሰዎች የሚማርኩ ወቅታዊ የሆኑ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን ይዘው ይወጣሉ።

◼ የሚወጡት ርዕሶች እጥር ምጥን ያሉ፣ ትምህርት ሰጪ፣ በሐቅ ላይ የተመሠረቱ፣ ከስሜታዊ ጥላቻና እውነቱን ከማጣመም ነፃ የሆኑ ናቸው።

◼ ማራኪ የሆኑት ስዕሎቻቸው ወዲያውኑ ፍላጎት የሚቀሰቅሱ ሲሆኑ ግልጽ የሆነው የአጻጻፍ ስልት ደግሞ ለማንበብ ጋባዥ ያደርጋቸዋል።

4 በስፋት አሰራጩዋቸው፦ መጽሔቶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማሰራጨት በአብዛኛው መግቢያዎችን በመዘጋጀት በኩል ባለን ትጋት፣ በምናወጣው ፕሮግራምና በስብከት እንቅስቃሴያችን መደራጀት ላይ የተመካ ነው። በመስከረም 1995 እና ጥቅምት 1996 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ያሉትን ተግባራዊ የሆኑ ሐሳቦች ብንከልስና ብንሠራባቸው መልካም ነው።

5 ከመጽሔቶቹ ይዘት ጋር በሚገባ ራስህን አስተዋውቅ፦ እያንዳንዱን እትም ስታነብ ይህንን ቅጂ ለማን ብሰጠው ጥሩ ነው ብለህ አስብ። በመግቢያህ ላይ ልትጠቀምበት የምትችል አንድ ነጥብ ወይም ጥቅስ ፈልግ። በርዕሱ ላይ ውይይት ለመጀመርና ፍላጎት ለመቀስቀስ የሚያስችልህ አንድ ጥያቄ ጠይቅ።

6 ከሰዎቹ ሁኔታ ጋር የሚስማማ አቀራረብ ይኑርህ፦ ወንድ፣ ሴት፣ በዕድሜ የገፋ ወይም ወጣት አለዚያም የምታውቀው ወይም እንግዳ ሰው ብታገኝ እንደሁኔታው አስተካክለህ ልታነጋግርበት የምትችል ቀለል ያለ አቀራረብ አዘጋጅ።

7 መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ንቁ ሁን፦ መጽሔቶቹ በቦርሳ፣ በእጅ ቦርሳ ወይም በኪስ ውስጥ በቀላሉ ሊያዙ ስለሚችሉ ስንጓዝም ሆነ ወደ ገበያ ስንሄድ ልንይዛቸው እንችላለን። ከዘመዶችህ፣ ከጎረቤቶችህ፣ ከሥራ ባልደረቦችህ፣ ከትምህርት ቤት ጓደኞችህ ወይም ከአስተማሪዎችህ ጋር በምታደርገው ውይይት አጋጣሚውን ተጠቅመህ አበርክትላቸው። በየሳምንቱ መጽሔት የምታበረክትበት አንድ ቀን መድብ።

8 ለመጽሔቶቹ አድናቆት አሳይ፦ መጽሔቶቹ ምንጊዜም ቢሆን ጠቃሚ ናቸው። መጽሔቶቹ የቆዩ ቢሆኑም እንኳ የያዙት መልእክት ተፈላጊነት አይቀንስም። በእጃችን ያሉትን መጽሔቶች ሁሉ ለማበርከት ልዩ ጥረት ካደረግን ቀደም ብለው የወጡት ቅጂዎች በመደርደሪያችን ላይ አይከማቹም።

9 የመንገድ ላይ ምስክርነት ውጤታማ ነው፦ ለብዙ ሰዎች መጽሔት ለማበርከት ዋናው ዘዴ በመንገድ ላይ የምንሰጠው ምሥክርነት ነው። አንዳንድ አስፋፊዎች በገበያ ቀኖች ሰው በሚበዛባቸው ቦታዎች የሚያገለግሉበት ቋሚ የሆነ ፕሮግራም አላቸው።

10 የንግድ ክልሎች ፍሬያማ ናቸው፦ ቤታቸው የማይገኙ ሰዎችን ከሱቅ ወደ ሱቅ በምንመሰክርበት ጊዜ እናገኛቸዋለን። አብዛኞቹ ነጋዴዎች ትሑቶች ሲሆኑ መጽሔቶችንም በደስታ ይቀበላሉ። በተለይ ስለ ንግድ ጉዳዮች የያዙ ርዕሶች ያላቸውን መጽሔቶች አበርክት።

11 የመጽሔት ደንበኞች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሊጀምሩ ይችላሉ፦ መጽሔቶቹ በወር ውስጥ ሁለት ጊዜ ስለሚታተሙ ላበረከትንላቸው ሰዎች ተመልሰን በመሄድ እንዳነበቡት መጠየቅና የሚቀጥለውን እትም ማስተዋወቅ ይገባናል። ተመላልሶ መጠየቅ የምናደርገው መጽሔቶችን ለማበርከት ብቻ ሳይሆን ሰውየው ለመጽሐፍ ቅዱስ ያለውን ፍላጎት ለማሳደግም መሆን አለበት። የመጽሔት ደንበኞች ማፍራት ወደፊት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚጀምሩ ሰዎች ለማግኘት የሚያስችል ግሩም አጋጣሚ ነው።

12 በሚያዝያና በግንቦት የምትችሉትን ሁሉ ጥረት አድርጉ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! በሚልዮን በሚቆጠሩ አድናቂ አንባቢዎች ዘንድ አመኔታ አትርፈዋል። መንግሥቱን ለማሳወቅ ውጤታማ በመሆናቸው ዘወትር በእጃችን ሊገኙና ባለን አጋጣሚ ሁሉ ልናበረክታቸው ይገባል። ሚያዝያና ግንቦት መጽሔቶች በብዛት የሚበረከቱባቸው ወሮች ይሆናሉ!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ