የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/95 ገጽ 2
  • ለምሥራቹ የሚገባ ጠባይ አሳዩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለምሥራቹ የሚገባ ጠባይ አሳዩ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለአምላክ ቤት አድናቆት አሳዩ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ሥርዓታማነት—ለአምላክ ያደሩ ሰዎች መለያ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ለይሖዋ የአምልኮ ቦታ አክብሮት አሳዩ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ሰዓት አክባሪ የመሆንን ልማድ አዳብሩ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 11/95 ገጽ 2

ለምሥራቹ የሚገባ ጠባይ አሳዩ

1 የይሖዋ ምሥክሮች እንደመሆናችን መጠን የይሖዋን ስም ለማስከበር እንፈልጋለን። ጠባያችን፣ የምንናገረው ነገር፣ የፀጉር አያያዛችንና አለባበሳችን ሰዎች ለእውነተኛው አምልኮ ባላቸው አመለካከት ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ እናውቃለን። በስብሰባዎቻችን ላይ ስንገኝ ደግሞ የዚህ እውነተኝነት የጎላ ነው። በስብሰባዎች ላይ የሚነገረውና የሚደረገው ሁሉ ለምሥራቹ የሚገባና ይሖዋን የሚያስከብር መሆን አለበት።— ፊልጵ. 2:4

2 በዓለም የሚታየው አብዛኛው የአለባበስና የፀጉር አያያዝ ልማድ በክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነት የለውም። ይህ ሁኔታ የምሥራቹ አገልጋዮች ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጡት የሚገባ ጉዳይ ነው። 11–110 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20 ላይ እንዲህ ይላል:- “ልብሶቻችን ውድ ዋጋ የሚያወጡ መሆን አያስፈልጋቸውም፣ ነገር ግን ንጹሕ፣ ማራኪና ልከኛ መሆን አለባቸው። ጫማችንም ቢሆን በደንብ የተጠገነና ጥሩ መልክ ያለው መሆን ይገባዋል። በተመሳሳይ በሁሉም ስብሰባዎች ላይ በመጽሐፍ ጥናትም ላይ ጭምር ሰውነታችን ንጹሕ መሆን ይኖርበታል። በንጽሕናና በተገቢ መንገድ የለበስንም መሆን ይገባናል።” በተጨማሪም አብዛኞቹ ልብሶች ጥሩ ሆነው እንዲታዩ መተኮስ ያስፈልጋቸዋል።

3 ሰዓት አክባሪነት የፍቅራዊ አሳቢነት አንዱ ምልክት ነው። ልናስወግዳቸው የማንችላቸው ነገሮች አልፎ አልፎ በስብሰባዎች ላይ በሰዓቱ እንዳንደርስ ሊያደርጉን ይችላሉ። ሁልጊዜ አርፍደን የምንደርስ ከሆነ ግን ለስብሰባዎቹ የተቀደሰ ዓላማ አክብሮት እንደሌለንና ሌሎችን እንዳንረብሽ መጠንቀቅ ያለብን መሆኑን እንዳልተገነዘብን ያሳያል። አርፋጆች ብዙውን ጊዜ የሌሎችን ሐሳብ ከመከፋፈላቸውም በላይ ከፕሮግራሙ የተሟላ ጥቅም እንዳያገኙ ያደርጓቸዋል። ሰዓት አክባሪነት በስብሰባው ላይ ለሚገኙ ሰዎች ስሜትና ፍላጎት አክብሮት እንዳለን ያሳያል።

4 ለሰዎች ያለን ፍቅር ስብሰባው በሚካሄድበት ጊዜ የሰዎችን ሐሳብ የሚከፋፍሉ ነገሮችን ከማድረግ እንድንቆጠብ ሊያደርገን ይገባል። ማንሾካሾክ፣ መብላት፣ ማስቲካ ማኘክ፣ ወረቀት ማንኮሻኮሽ፣ ሳያስፈልግ ወደ መጸዳጃ ቤት መሄድ የሌሎችን ትኩረት ከመሳቡም በተጨማሪ የይሖዋ አምልኮ ቦታ ሊሰጠው የሚገባውን ክብር ያሳጣዋል። ወንድሞች ከመቀመጫቸው እንዲነሱ የሚያስገድዱ አንዳንድ ድንገተኛ ሁኔታዎች እስካልተፈጠሩ ድረስ የጉባኤ ሥራዎችን ማከናወንም ሆነ ከሌሎች ጋር ማውራት ተገቢ አይደለም። እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች እስካልተከሰቱ ድረስ ሁሉም ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን መጥቀም እንዲችሉ ተቀምጠው ፕሮግራሙን በጥሞና መከታተል አለባቸው። ‘ፍቅር የማይገባውን ስለማያደርግ’ መጥፎ ጠባዮች በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ ቦታ የላቸውም።— 1 ቆሮ. 13:4, 5፤ ገላ. 6:10

5 ልጆቻችን በስብሰባዎች ላይ የሚያሳዩት መልካም ጠባይም ለይሖዋ ስም ውዳሴና ክብር ያመጣል። ወላጆች ልጆቻቸውን በቅርብ ሊከታተሏቸው ያስፈልጋል። ልጆች እንዲያዳምጡና ተሳትፎ እንዲያደርጉ ሊበረታቱ ይገባል። ትንንሽ ልጆች ያሏቸው ብዙ ወላጆች ሌሎችን ብዙም ሳይረብሹ ከመንግሥት አዳራሹ በመውጣት ለልጆቻቸው የሚያስፈልገውን ነገር ማድረግ በሚያስችላቸው ቦታ ለመቀመጥ መርጠዋል።

6 ጳውሎስ “ለምሥራቹ የሚገባ ጠባይ አሳዩ” በማለት አጥብቆ መክሯል። (ፊልጵ. 1:27 አዓት) እንግዲያው በስብሰባዎች ላይ ስንገኝ ጥሩ ጠባይና ለሌሎች አሳቢነት ለማሳየት ጥረት እናድርግ። እያንዳንዱ ሰው የሚያደርገው ትብብር “አንዳችን በሌላው እምነት እርስ በርስ ለመበረታታት” ያስችለናል።— ሮሜ 1:12 አዓት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ