የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/96 ገጽ 1
  • በሙሉ ነፍስ አገልግሉ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በሙሉ ነፍስ አገልግሉ!
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይሖዋ በሙሉ ነፍስ የምታቀርቡትን አገልግሎት ከፍ አድርጎ ይመለከተዋል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ይሖዋን በሙሉ ነፍስ ማገልገል
    ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
  • ይሖዋን በሙሉ ነፍስ ማገልገል
    ለይሖዋ ዘምሩ
  • መደበኛ ባልሆነ መንገድ መመሥከር ትችላላችሁ!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
km 5/96 ገጽ 1

በሙሉ ነፍስ አገልግሉ!

1 ይሖዋን የምናመሰግንባቸው በጣም ብዙ ምክንያቶች አሉን። ከእነዚህም መካከል ይሖዋ ከዚህ በፊት ያደረገልን፣ አሁን እያደረገልን ያለውና ወደ ፊት የሚያደርግልን ነገሮች ይገኙበታል። አመስጋኝነታችን ምን እንድናደርግ ሊገፋፋን ይገባል? የዳዊት መዝሙር “እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፣ ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው” በማለት መልስ ይሰጣል።— መዝ. 34:1

2 መጽሐፍ ቅዱስ ስበኩ ተብለን እንደታዘዝን በግልጽ ያሳያል። ይህም “ለይሖዋ እንደምናደርገው በሙሉ ነፍስ” የምናከናውነው ሥራ ነው። (ቆላ. 3:23 አዓት) በእርግጥ በሙሉ ነፍስ የምናገለግል ከሆነ በአገልግሎቱ ምን ያህል እንሳተፋለን? ይሖዋ ለእኛ ያሳየውን ፍቅር ስንመለከት ስለ እርሱና ስለ ታላላቅ ዓላማዎቹ ለሰዎች በመናገሩ ሥራ ሙሉ በሙሉ እንድንካፈል ልባችን እንደሚገፋፋን አያጠራጥርም! የቻልነውን ያህል ለመሥራት እንነሳሳለን።

3 በሙሉ ነፍስ የሚያገለግል አንድ ሰው በቅዱስ አገልግሎት ላይ ለማተኮር ይፈልጋል ብሎ መጠበቁ ምክንያታዊ ነው። ይህ ፍላጎት ያደረበት መዝሙራዊ “ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ” ብሏል። (መዝ. 119:164) እንደ መዝሙራዊው የሚሰማቸው ሰዎች ይሖዋን ለማወደስ የሚያስችል አጋጣሚ ሲፈጠር ይጠቀሙበታል። ሁኔታቸው በፈቀደላቸው መጠን የተቻላቸውን ያህል በቅንዓት ያገለግላሉ።

4 ይሖዋን ለማወደስ የሚያስችሉ ብዙ አጋጣሚዎች አሉን፦ ምሥራቹን ለመስበክ ከቤት ወደ ቤት እስከምንሄድ ድረስ እጃችንን አጣጥፈን መጠበቅ አይኖርብንም። የሥራ ባልደረቦቻችን፣ የትምህርት ቤት ጓደኞቻችን፣ ዘመዶቻችንና የምናውቃቸው ሰዎች ሁሉ የመንግሥቱን መልእክት መስማት ያስፈልጋቸዋል። በጉዞ ላይ ሳለን ከሰዎች ጋር ውይይት መጀመር እንችላለን፤ ይህም ለሆቴል፣ ለምግብ ቤትና ለነዳጅ ማደያ ሠራተኞች ወይም ለታክሲ ሾፌሮች ለመመስከር ያስችላል። እቤት በምንሆንበት ጊዜ ለጎረቤቶቻችን ወይም ዕቃ ለመሸጥ ወደ ቤታችን ለሚመጡ ሰዎች መመስከር እንችላለን። ሆስፒታል ከገባን ለነርሶች ለዶክተሮችና ለሌሎች በሽተኞች መደበኛ ባልሆነ መንገድ መስበክ እንችላለን።

5 መደበኛ ባልሆነ መንገድ የሚሰጥ ምስክርነት ፍሬ ያስገኛል፦ አንድ ቀን ሁለት የይሖዋ ምሥክሮች በአንድ መናፈሻ ውስጥ በእግራቸው እየተጓዙ ሳሉ ልጁን ያንሸራሽር ከነበረ አንድ ወጣት ጋር ውይይት ጀመሩ። በኋላም ይህ ወጣትና ባለቤቱ እውነትን ተቀበሉ። ወጣቱ ከሁለቱ የይሖዋ ምሥክሮች ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ከመገናኘቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ‘አምላክ ሆይ ካለህ እባክህ እንዳውቅህ እርዳኝ’ በማለት ጸልዮ እንደነበር ከጊዜ በኋላ ገልጿል። መናፈሻው ውስጥ ከእነርሱ ጋር መገናኘቱ ይሖዋ ለጸሎቱ የሰጠው ምላሽ እንደሆነ አድርጎ ይመለከተዋል።

6 ሰዎችን በመንፈሳዊ ለመርዳት በሙሉ ነፍሳቸው የሚያገለግሉ ወንድሞች ከፍተኛ ደስታ ያገኛሉ። እንዲህ ያለው “በፍጹም ልብ” የሚቀርብ አገልግሎት ይሖዋን እንደሚያስደስተው ያውቃሉ።— 1 ዜና 28:9

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ