የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/98 ገጽ 7
  • አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
  • አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 10/98 ገጽ 7

አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም

1 መስከረም ላይ የሚጀምረው የሁለት ቀናት የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም ጭብጥ “የአምላክን ትእዛዛት ጠብቁ በሕይወትም ትኖራላችሁ” የሚል ነው። (ምሳሌ 4:4) ስብሰባው የአምላክን ትእዛዛት መጠበቅ ከባድ የማይሆንበትን ምክንያት ጎላ አድርጎ ይገልጻል። ከዚህም በላይ የአምላክን ፈቃድ ማድረግ እርካታና እውነተኛ ደስታ እንዲሁም ተስፋ የሚያስገኘው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።—ማቴ. 11:28-30፤ ዮሐ. 13:17

2 ክርስቶስ የሰጠውን ትእዛዝ በመከተል በስብሰባው ላይ ለመጠመቅ የሚፈልጉ ሁሉ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹን ማነጋገር ይኖርባቸዋል። እርሱም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ያደርጋል።—ማቴ. 28:19, 20

3 በስብሰባው ላይ የሚቀርበው ሲምፖዚየም ለአምላክና ለወንድሞቻችን ፍቅር ማሳየት የምንችልባቸውን ተግባራዊ የሆኑ መንገዶች ይዘረዝራል። (ዮሐ. 13:34, 35፤ 1 ዮሐ. 5:3) መዝሙር 19 እና 119 ላይ የሚገኙ ልብ የሚነኩ ምክሮች በፕሮግራሙ ውስጥ ተካትተዋል። በእነዚህ መዝሙራት ውስጥ የሚገኙት በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉ ማሳሰቢያዎች የሰፈሩት ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ቢሆንም በዛሬው ጊዜ የምንኖረውን እንዴት በግል እንደሚጠቅሙን እንመለከታለን።

4 የአውራጃ የበላይ ተመልካቹ የሚያቀርበው የሕዝብ ንግግር “አምላክን ፍሩ ትእዛዛቱንም ጠብቁ” የሚል ርዕስ ያለው ይሆናል። (መክ. 12:13) የወረዳ የበላይ ተመልካቹ የሚያቀርበው የመጨረሻ ንግግር በዛሬው ጊዜ ያሉት ወጣቶች ሕይወታቸውን በተሻለ መንገድ እንዴት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉና ወደፊት የሚመጣውን ዘላለማዊ ሕይወት በልበ ሙሉነት መጠባበቅ የሚችሉት ለምን እንደሆነ የሚገልጽ ይሆናል። የአውራጃ የበላይ ተመልካቹ ‘የንጉሥ ሕግ’ በተባለው ፍቅር መኖር የሚያስገኛቸውን በርካታ ጥቅሞች በመዘርዘር ፕሮግራሙን ይደመድማል። (ያዕ. 2:8) በእርግጥም ይህ ማንኛችንም ሊያመልጠን የማይገባ ፕሮግራም ነው!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ