ወደ 6,000 ምን ያህል እንጠጋ ይሆን?
ባለፈው የአገልግሎት ዓመት ማብቂያ ላይ 5,649 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር በማግኘታችን በጣም ተደስተን ነበር። ይሁን እንጂ በዚያን ጊዜም በአገራችን ውስጥ ከ5,800 በላይ አስፋፊዎች ነበሩ። በዚህ መሃል ከመንግሥት ዜና ስርጭትና ከመታሰቢያው በዓል ጋር በተያያዘ ይሖዋን ማገልገል የጀመሩ አዳዲስ አስፋፊዎች አሉ። ይህም በመሆኑ በያዝነው የአገልግሎት ዓመት ማብቂያ ላይ ወደ 6,000 የአስፋፊዎች ቁጥር እንጠጋ ይሆን የሚል ጥያቄ ይነሳል። በጉባኤው ውስጥ ያለ እያንዳንዱ አስፋፊ በነሐሴ ወር ውስጥ በአገልግሎት ለመካፈል ቁርጥ ዝግጅት ካደረገና የአገልግሎት ሪፖርቱን ሳይዘገይ ከመለሰ ሊደረስበት ይችላል። የወሩ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት ቅዳሜና እሁድ ላይ ስለሚውሉ ከእነዚህ ቀናት አንስቶ በመስክ አገልግሎት ለመካፈል ለምን ዕቅድ አታወጣም? ከወሩ መጀመሪያ አንስቶ በአገልግሎት በመካፈል በነሐሴ ወር ውስጥ በምሥክርነቱ ሥራ ይነስም ይብዛ የተወሰነ ሰዓት ማሳለፍ እንችላለን። ጥረታችንን በማስተባበር ወደ 6,000 የሚጠጋ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ማግኘት እንችላለን። ይህ ለይሖዋ የሚቀርብ በጣም የሚያስተጋባ ውዳሴ ይሆናል!—መዝ. 47:1