የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/98 ገጽ 1
  • ደጋግመን መሄድ አለብን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ደጋግመን መሄድ አለብን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “የአገልግሎት ክልላችንን ደጋግመን ሸፍነናል!”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ያለማቋረጥ ተመልሰን የምንሄደው ለምንድን ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • በተደጋጋሚ የምንሄደው ለምንድን ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • እንዴት ይሰማሉ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
km 12/98 ገጽ 1

ደጋግመን መሄድ አለብን

1 ምሥራቹ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተነገራችሁ አዎንታዊ ምላሽ ሰጥታችኋልን? ካልሆነ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት እስክትስማሙ ድረስ የይሖዋ ምሥክሮች ደጋግመው በመምጣታቸው አመስጋኝ መሆን አለባችሁ። የተመደበላችሁን የአገልግሎት ክልል ደጋግማችሁ ስትሠሩ ይህን ነገር ማስታወሳችሁ ጥሩ ነው።

2 ሰዎች በሕይወታቸው ተለዋዋጭ ነገር ይገጥማቸዋል። አዳዲስ ችግሮች ወይም ሁኔታዎች ይከሰታሉ፣ በአካባቢያቸው ወይም በዓለም ላይ ስለተደረጉ አሳዛኝ ነገሮች ይሰማሉ፣ የኢኮኖሚ ኪሳራ ይደርስባቸዋል አሊያም በቤተሰባቸው ውስጥ አንድ ሰው ይታመማል ወይም ይሞታል። እነዚህ ነገሮች፣ የችግሮቹን መንስዔ ለማወቅ እንዲፈልጉ ያነሳሷቸው ይሆናል። በሰዎች አእምሮ ውስጥ የሚጉላሉትን ጉዳዮች ለይተን ካወቅን በኋላ የሚያጽናና መልእክት ልንነግራቸው ይገባል።

3 ይህ የነፍስ አድን ሥራ ነው፦ አደጋ በደረሰበት አካባቢ ስለሚገኙ ነፍስ አድን ሠራተኞች እስቲ አስብ። ምንም እንኳ አንዳንዶቹ ፍለጋ የሚያደርጉት ጥቂት ተራፊዎች ብቻ እየተገኙ ባለበት ቦታ ቢሆንም በሌላው አካባቢ ያሉ የሥራ ባልደረቦቻቸው በርካታ ተራፊዎችን እያገኙ እንዳሉ ስለሚያውቁ ከመፈለግ ወደኋላ አይሉም ወይም ፍለጋቸውን አያቆሙም። የነፍስ አድን ተልዕኳችን ገና አላበቃም። በየዓመቱ “ከታላቁ መከራ” በሕይወት ለመትረፍ የሚፈልጉ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተገኙ ነው።—ራእይ 7:9, 14

4 “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።” (ሮሜ 10:13–15) እነዚህ ቃላት ለሁላችንም በስብከቱ ሥራ የመጽናትን አስፈላጊነት ሊያስታውሱን ይገባል። የአገልግሎት ክልላችን መጀመሪያ ከቤት ወደ ቤት መንኳኳት ሲጀምር ሕፃናት የነበሩ ልጆች አድገው ስለ ወደፊት ሕይወታቸውና ስለ ሕይወት ዓላማ በጥሞና ማሰብ የሚችሉበት ዕድሜ ላይ ደርሰዋል። ከጊዜ በኋላ ማን ተቀባይ ሊሆን እንደሚችል አናውቅም። (መክ. 11:6) በፊት ተቃዋሚዎች የነበሩ ብዙዎች እውነትን ተቀብለዋል። የእኛ ሥራ በሰዎች ላይ መፍረድ ሳይሆን ሰዎች የሚሰሙበትንና ከዚህ አሮጌ ዓለም በሕይወት የሚተርፉበትን አጋጣሚ መስጠታችንን መቀጠል ነው። የመጀመሪያዎቹ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እንዳደረጉት ወደ ሰዎች ‘ያለማቋረጥ እየሄድን’ ለመንግሥቱ መልእክት ፍላጎት እንዲያሳድሩ ለማነሳሳት መጣር ይኖርብናል።—ማቴ. 10:6, 7 NW

5 ይሖዋ እስከዛሬ ድረስ እንሰብክ ዘንድ በሩን ክፍት ማድረጉ የምሕረቱ መግለጫ ነው። (2 ጴጥ. 3:9) ሰዎች መልእክቱን ደጋግመው እንዲሰሙ ማድረጋችን የአምላክ ፍቅር ጎልቶ እንዲታይ የሚያደርግ ከመሆኑም ሌላ እሱን የምናወድስበት መንገድ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ