የተወሰነ የመጽሔት ትእዛዝ አለህ?
1 ወደ መስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ ሄደህ የአገልግሎት ቦርሳህን ስትከፍት መጽሔቶች አለመያዝህን የተገነዘብክበት ቀን አለ? እንግዲያው “መጽሔቶቻችንን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙባቸው” የሚል ርዕስ የያዘውን የመስከረም 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ አስታውስ። አባሪው “የተወሰነ የመጽሔት ትእዛዝ ይኑርህ” በማለት የሚከተለውን ገልጾ ነበር:- “ከእያንዳንዱ እትም ምን ያህል መጽሔቶችን እንደምትፈልግ ለመጽሔት አገልጋዩ ንገረው፤ ልታበረክተው የምትችለውን ያክል ብቻ እዘዝ። በዚህ መንገድ አንተም ሆንክ ቤተሰብህ በቂ መጠን ያላቸው መጽሔቶች ሳያቋርጡ ይደርሷችኋል።” እንደዚያ አድርገሃል?
2 የተወሰነ መጠን ያለው መጽሔት ለምን አታዝዝም? እንዲህ በማድረግህ በየሳምንቱ መጽሔቶቹን ለማሰራጨ የበለጠ ኃላፊነት የሚሰማህ ከመሆኑም በላይ ተጨማሪ ደስታ ታገኛለህ። አስቀድሞም ቋሚ የመጽሔት ትእዛዝ ካለህ በአገልግሎት ለምታሳልፈው አማካኝ የወር እንቅስቃሴ በቂ መሆን አለመሆኑን በድጋሚ ገምግም። በየሳምንቱ ያዘዝነውን መጽሔት በመውሰድ ረገድ ታማኝ መሆን እንደምንፈልግና እንዲህ የማድረግ ግዴታ ሊሰማንም እንደሚገባ የታወቀ ነው። ረዘም ላለ ጊዜ ከጉባኤ ርቀህ የምትሄድ ከሆነ እስክትመለስ ድረስ የመጽሔት አገልጋዩ መጽሔቶችህን ለሌላ ሰው እንዲሰጥ የምትፈልግ ከሆነ አሳውቀው።
3 ከላይ የተጠቀሰው አባሪ ‘ቋሚ የመጽሔት ማበርከቻ ቀን መመደብ’ እንዳለብንም ተናግሮ ነበር። ለሳምንታዊው የመጽሔት ቀን ድጋፍ መስጠት ትችላለህ? በ1999 የይሖዋ ምሥክሮች ቀን መቁጠሪያ ላይ እንደወጣው ዓመቱን በሙሉ በእያንዳንዱ ቅዳሜ የመጽሔት ቀን ይኖራል! መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔት የማሰራጨቱን አስፈላጊነት አቅልለህ አትመልከተው። በመጽሔት እንቅስቃሴ የተሟላ ተሳትፎ ለማድረግ ስንጥር ለሰዎች ‘የመልካምን ወሬ ምስራች መናገራችን’ ነው።—ኢሳ. 52:7