የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/01 ገጽ 1
  • ዓላማው ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዓላማው ምንድን ነው?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ተማሪዎችን ከስማችን በስተጀርባ ወዳለው ድርጅት መምራት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ሌሎች ሰዎች በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ እርዷቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • “ወደ ይሖዋ ቤት እንሂድ”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
  • እውቀት በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት ደቀ መዛሙርት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
km 10/01 ገጽ 1

ዓላማው ምንድን ነው?

1 ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ የምናስጠናበት ዓላማ ምንድን ነው? እንዲሁ እውቀት ለማስጨበጥ፣ የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ ለመርዳት ወይም ስለወደፊቱ ጊዜ ያላቸውን አመለካከት ብሩህ ለማድረግ? አይደለም። ዋነኛ ዓላማችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ መርዳት ነው! (ማቴ. 28:19፤ ሥራ 14:21) መጽሐፍ ቅዱስ የምናስጠናቸው ሰዎች በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘት የሚያስፈልጋቸው በዚህ ምክንያት ነው። በመንፈሳዊ እንዲያድጉ ከተፈለገ ስለ ክርስቲያናዊው ድርጅት ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል።

2 ይህንን ማድረግ የምትችሉበት መንገድ:- ከመጀመሪያው ጀምሮ ተማሪው በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ እንዲገኝ ዘወትር አበረታቱት። (ዕብ. 10:24, 25) እነዚህ ስብሰባዎች እንዴት እምነቱን እንደሚያጠነክሩለትና የአምላክን ፈቃድ እንዲያደርግ እንደሚረዱት እንዲሁም ይሖዋን ከሚያወድሱ ከሌሎች ጋር የሚያንጽ ጊዜ ለማሳለፍ የሚያስችል አጋጣሚ እንደሚፈጥሩለት ግለጹለት። (መዝ. 27:13፤ 32:8፤ 35:18) ለጉባኤውና ለስብሰባዎች ያላችሁን ፍቅርና አድናቆት የምትገልጹበት መንገድ በስብሰባዎች ላይ የመገኘት ፍላጎቱን ሊቀሰቅሰው ይችላል።

3 አዲሶች የይሖዋ ድርጅት ዓለም አቀፋዊ የወንድማማች ማኅበር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋቸዋል። የይሖዋ ምሥክሮች​—⁠ከስሙ በስተጀርባ ያለው ድርጅት እና መላው የወንድማማች ማህበር የተባሉትን ቪዲዮዎች አሳዩአቸው። ይሖዋ በመላው ዓለም በሚልዮን የሚቆጠሩ ለእርሱ ያደሩ ሰዎችን ፈቃዱን ለማስፈጸም እየተጠቀመባቸው እንዳለ እንዲገነዘቡ እርዷቸው። እነርሱም አምላክን እንዲያገለግሉ ግብዣ እንደቀረበላቸው ይወቁ።​—⁠ኢሳ. 2:2, 3

4 አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ እውነተኛ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ሲሆን ማየት ከፍተኛ ደስታ ይሰጣል። ዓላማችን ይሄ ነው!​—⁠3 ዮሐ. 4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ