መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1, 2001
አንድ የሚያሳዝን ዜና ከጠቀስክ በኋላ እንዲህ ብለህ ጠይቅ:- “ሰዎች ይህን ዓይነት ክፉ ነገር የሚያደርጉት ለምንድን ነው? ሁላችንም መልካሙን ከክፉው መለየት ያለብን ቢሆንም ሰዎች አሁንም መጥፎ ነገሮችን ያደርጋሉ። ይህ የሆነው ለምንድን ነው? [የሚሰጠውን መልስ ካዳመጥክ በኋላ ራእይ 12:9ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ሕሊናችንን በመጠበቅ እንዴት መጥፎ ነገር ከማድረግ መራቅ እንደምንችል ያብራራል።”
ንቁ!® ኅዳር 2001
“በዛሬው ጊዜ ሰዎች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ጭንቀት ውስጥ እየኖሩ ነው ቢባል ይስማማሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል አስቀድሞ ተናግሯል። [2 ጢሞቴዎስ 3:1ን አንብብ።] ብዙ ሰዎች ሕይወት ከባድ ስለሚሆንባቸው ተስፋ ይቆርጣሉ። ይህ መጽሔት እውነተኛ ማበረታቻ የሚሰጥ ሲሆን የተስፋ መቁረጥን ስሜት መቋቋምና ሕይወትን አስደሳች ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።”
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 15, 2001
“‘ኢየሱስ ለእኛ ሞቶልናል’ ሲባል እንሰማለን። [ዮሐንስ 3:16ን ጥቀስ።] የአንድ ሰው መሞት እንዴት ሁላችንንም ሊያድን እንደሚችል አስበው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ የሆነ መልስ የሚሰጥ ሲሆን “ኢየሱስ ያድናል—እንዴት?” የሚለው ይህ ርዕስ ስለዚህ ሐሳብ ጥሩ ማብራሪያ ይሰጣል።”
Nov. 22
“የሰው ልጆች አካባቢያቸውን ለመንከባከብ የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነውን? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ብዙዎች እንክብካቤ የሚያሻው የምድራችን የተፈጥሮ ሚዛን ሳይዛባ እስከ መጨረሻው የመዝለቁ ጉዳይ በእጅጉ ያሳስባቸዋል። ደስ የሚለው ግን አምላክ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶታል። [ነህምያ 9:6ን አንብብ።] ይህ ንቁ! መጽሔት በምድር ላይ ያለው ሕይወት የወደፊት ተስፋ ምን እንደሆነ ይናገራል።