ለመስክ አገልግሎት የሚሆኑ አቀራረቦች
በቅርብ አስቀምጡት
ይህንን አባሪ እንዴት መጠቀም ይቻላል?
ቀጥሎ ካሉት አቀራረቦች ውስጥ አብዛኞቹ ቀደም ባሉት የመንግሥት አገልግሎታችን እትሞች ላይ የወጡ ናቸው። ምሥክርነቱን ስትሰጥ ከእነዚህ አቀራረቦች ውስጥ የቻልከውን ያህል ተጠቀምና ያገኘኸውን ውጤት ተመልከት። ይህን አባሪ በቅርብ አስቀምጠህ ለአገልግሎት ስትዘጋጅ ተጠቀምበት።
ቶሎ ወደ ነጥቡ ከገባህ ግለሰቡ ለአምላክ ቃል ያለውን ፍላጎት መቀስቀስ ትችላለህ። ቀጥተኛ የሆነ ጥያቄ ካቀረብክ በኋላ አጠር ያለ ቅዱስ ጽሑፋዊ መልስ አንብብ። እነዚህን አቀራረቦች ልትሞክራቸው ትችላለህ፦
“ስለ ወደፊቱ ጊዜ ሲያስቡ የሚታይዎት ብሩህ ተስፋ ነው ወይስ የጨለመ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ አሁን ስለምናያቸው ምስቅልቅል ሁኔታዎችና እነሱ ስለሚያስከትሉት ውጤት አስቀድሞ ተንብዮአል።”—2 ጢሞ. 3:1, 2, 5፤ ምሳሌ 2:21, 22
“በዛሬው ጊዜ የጤና ጉዳይ በጣም አሳሳቢ ሆኗል። አምላክ ማንኛውንም ዓይነት የጤና ችግሮች ለዘለቄታው ለማስወገድ ቃል እንደገባ ያውቃሉ?”—ኢሳ. 33:24፤ ራእይ 21:3, 4
“መጽሐፍ ቅዱስ ወደፊት መላውን ዓለም የሚያስተዳድር አንድ ብቸኛ መንግሥት እንደሚመጣ አስቀድሞ እንደተነበየ ያውቃሉ?”—ዳን. 2:44፤ ማቴ. 6:9, 10
“ኢየሱስ ክርስቶስ ምድርን ቢያስተዳድር ኖሮ ሁኔታዎች ምን መልክ ይኖራቸዋል ብለው ያስባሉ?”—መዝ. 72:7, 8
“ብዙ ሰዎች በጾታ፣ በሃይማኖት ወይም በዘር የተነሳ መድልዎ ይደረግባቸዋል። አምላክ እንዲህ ዓይነቱን ሁኔታ እንዴት የሚመለከተው ይመስልዎታል?”—ሥራ 10:34, 35
“ኢየሱስ ክርስቶስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት ብዙ ተአምራትን እንዳደረገ እናውቃለን። አንድ ተጨማሪ ተአምር እንዲፈጽም የመጠየቅ አጋጣሚ ቢያገኙ ምን እንዲያከናውን ይጠይቁት ነበር?”—መዝ. 72:12-14, 16
“ብዙ ሰዎች ስለ ችግር መስማት ሰልችቷቸዋል። መስማት የሚፈልጉት መፍትሔውን ነው። ይሁን እንጂ ለችግሮቻችን እውነተኛ መፍትሔ ማግኘት የምንችለው ከየት ነው?”—2 ጢሞ. 3:16, 17
“በጌታ (ወይም አባታችን ሆይ በተባለው) ጸሎት ውስጥ የሚጸልዩለት መንግሥት የቱ እንደሆነ ያውቃሉ?”—ራእይ 11:15
[ገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
ውይይት መክፈቻ ሐሳቦች
ቀጥሎ የተዘረዘሩት ጥያቄዎች በማመራመር መጽሐፍ ውስጥ ከሚገኙ ርዕሶች የተውጣጡ ሲሆኑ በመጽሐፉ ውስጥ የእያንዳንዱ ጥያቄ መልስ የሚገኝበት ገጽ በቅንፍ ተቀምጧል።
የምናረጀውና የምንሞተው ለምንድን ነው? (98)
ሙታን በምን ሁኔታ ይገኛሉ? (99)
በአምላክ መኖር ለማመን የሚያበቁ ጥሩ ምክንያቶች አሉን? (146)
አምላክ በሰው ልጆች ላይ ስለሚደርሰው ነገር ግድ አለውን? (147)
አምላክ በእርግጥ የተወሰነ አካል ነውን? (148)
ጥሩ ሰዎች ሁሉ ወደ ሰማይ ይሄዳሉን? (162)
አንድ ሰው እውነተኛ ደስታ ያለበት ሕይወት እንዲያገኝ ወደ ሰማይ መሄድ ይኖርበታልን? (163)
የአምላክን የግል ስም ማወቅና መጠቀም ያስፈለገው ለምንድን ነው? (197)
ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ራሱ ነውን? (213)
የአምላክ መንግሥት ወደፊት ምን ታከናውናለች? (228)
የሰብዓዊ ሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? (243)
ትዳርን ለማሻሻል ምን ነገሮች ሊረዱ ይችላሉ? (253)
ሃይማኖቶች ሁሉ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አላቸውን? (321)
አንድ ሰው ትክክለኛው ሃይማኖት የትኛው እንደሆነ እንዴት ሊያውቅ ይችላል? (327)
ሰይጣን በአሁኑ ዓለም ውስጥ ምን ያህል ኃያል ነው? (363)
አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው? (392)
ክፋት ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው? (427)
ይህን ዓለም የሚገዛው ማን ነው? አምላክ ወይስ ሰይጣን? (436)