መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት እንችላለን?
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1
“በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ምስሎችን በአምልኳቸው የሚጠቀሙ ሲሆን ሌሎች በሚልዮን የሚቆጠሩ ደግሞ እንዲህ ማድረጉ ስህተት እንደሆነ ይሰማቸዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የአምላክ አመለካከት ምንድን ነው ብለው አስበው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ዮሐንስ 4:24ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀም እንዴት እንደተጀመረና መጽሐፍ ቅዱስ ምስልን ለአምልኮ መጠቀምን በሚመለከት ምን እንደሚል ይገልጻል።”
ንቁ! ሐምሌ 2002
“በምድር ላይ የሚኖር ሁሉም ሰው እውነተኛ ነጻነት ማግኘት የሚችል ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አምላክ የሰጠንን ይህንን አስደሳች ተስፋ ይመልከቱ። [ሮሜ 8:21ን አንብብ።] ይህ ተስፋ እውን እንዲሆን ማንኛውም ዓይነት ባርነት መወገድ እንደሚኖርበት አይስማሙም? ይህ የንቁ! እትም አምላክ የሰጠው ተስፋ እንዴት እውን እንደሚሆን ይነግረናል።”
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 15
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ
“ክፉ ሰዎች በሲኦል ቅጣት ይደርስባቸዋል ብለው ያምናሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ የኃጢአት ቅጣት ምን እንደሆነ በግልጽ ይናገራል። [ሮሜ 6:23 የመጀመሪያውን ሐረግ አንብብ።] እንግዲያው ሲኦል እሳታማ የመሠቃያ ቦታ ነው? ወይስ ከአምላክ መራቅን የሚያመለክት ምሳሌያዊ አገላለጽ? ይህ መጽሔት ለእነዚህ ጥያቄዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ መልስ ይሰጣል።”
July 22
“ብዙ ሰዎች ቁማርን ምንም ጉዳት የሌለው የጊዜ ማሳለፊያ እንደሆነ አድርገው ይመለከቱታል። ሌሎች ደግሞ ቁማር ቤተሰብንና ኅብረተሰብን ይጎዳል የሚል አመለካከት አላቸው። ይህ የንቁ! እትም በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶችን መሠረት በማድረግ ቁማርን የሚመለከት ማብራሪያ ይሰጣል። እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ቁማርን በተመለከተ ምን እንደሚል ማወቅ ይፈልጉ ይሆናል።” ለምሳሌ 1 ጢሞቴዎስ 6:10ን አንብብ።