መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1
“ሁላችንም የመውደድና የመወደድ ተፈጥሯዊ ፍላጎት አለን። [በገጽ 4 ላይ የሚገኘውን ስዕል መግለጫ አንብብ።] በዛሬው ጊዜ ግን ሰዎች ቅድሚያ የሚሰጡት ለሌሎች ነገሮች እንደሆነ አስተውለዋል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት እውነተኛ ፍቅር ምን ማለት እንደሆነና እንዴት ማዳበር እንደሚቻል ያብራራል።” 1 ቆሮንቶስ 13:2ን አንብብ።
ንቁ! ሐምሌ 2003
“ብዙዎቻችን የስኳር ሕመምተኛ የሆኑ የምናውቃቸው ሰዎች ይኖራሉ። ለመሆኑ ስለዚህ ሕመም ምን ያህል ያውቃሉ? [መጽሔቱን አሳየውና መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት ለስኳር ሕመም ምክንያት የሚሆኑትን ነገሮችና ሕክምና ማግኘት የሚቻልበትን መንገድ ይገልጻል። ከዚህም በላይ መጽሐፍ ቅዱስ ከማንኛውም ዓይነት ሕመም ዘላቂ ፈውስ እንደምናገኝ የሚሰጠውን ተስፋ ያብራራል።” ኢሳይያስ 33:24ን በማንበብ ደምድም።
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 15
“ብዙ ሰዎች ራስን የማግለል ዝንባሌ እየተስፋፋ እንደመጣ ይሰማቸዋል። እንዲህ ዓይነቱ ዝንባሌ ጥሩ ይመስሎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ጓደኝነት ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ ይህ ጥቅስ ምን እንደሚል ይመልከቱ። [መክብብ 4:9, 10ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ወዳጆች ለምን እንደሚያስፈልጉንና ራስን የማግለልን ባሕርይ እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል ያብራራል።”
July 22
“ብዙ ሰዎች እርቃንን የሚያሳዩ ምስሎች በቀላሉ የሚገኙ መሆናቸው ያሳስባቸዋል። ይህ ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነ ይሰማዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ጠቃሚ ምክር ከአደጋ ሊጠብቀን ይችላል። [ኤፌሶን 5:3, 4ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ከዚህ ስውር አደጋ ራሳችንን መጠበቅ የምንችልበትን መንገድ ይገልጻል።”