መጽሔቶቻችንን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“አንዳንድ ሰዎች አምላክን ለማምለክ የአንድ ሃይማኖታዊ ድርጅት አባል መሆን አስፈላጊ እንዳልሆነ ይሰማቸዋል። ይህን ጉዳይ አስበውበት ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት አምላክ በጥንት ጊዜያት ከሰዎች ጋር ስለነበረው ግንኙነት የሚናገሩ ታሪካዊ ዘገባዎችን ይመረምራል። እንዲሁም አምላክን በእውነት ማምለክ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ያብራራል።” ዮሐንስ 4:24ን አንብብ።
ንቁ! ሰኔ 2004
“የሕክምናው ሳይንስ በሽታን በመዋጋት ረገድ አስደናቂ እድገት አድርጓል፤ ሆኖም በሽታ ከዓለም ላይ ሙሉ በሙሉ የሚወገድበትን ጊዜ ለማየት የምንታደል ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት በኢሳይያስ 33:24 ላይ ያለው ትንቢት ሲፈጸም በምድር ላይ የሚኖር ሁሉ የተሟላ ጤንነት እንደሚኖረው ይናገራል።” ከዚያም ጥቅሱን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 15
“በዘመናችን ልጆችን ማሰልጠን ትግል ይጠይቃል ቢባል አይስማሙም? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ቢሆንም ወላጆች ልጆችን በማሰልጠን ረገድ ሊሳካላቸው እንደሚችል የሚናገውን ይህን ማበረታቻ ይመልከቱ። [ምሳሌ 22:6ን አንብብ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ወላጆች ልጆችን ማሰልጠን የሚጠይቀውን ፈታኝ ሁኔታ ለመወጣት እንዲችሉ የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮችን ይዟል።”
Awake! June 22
“አንዳንድ ሰዎች አምላክ አለ የሚለው አመለካከት ሳይንሳዊ ድጋፍ እንደሌለው ይሰማቸዋል። ሆኖም ሳይንስ ራሱ የፈጣሪን መኖር ይደግፋል ብለው የሚናገሩ ሳይንቲስቶች እንዳሉ ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ የንቁ! መጽሔት እትም እነዚህ ሳይንቲስቶች እዚህ መደምደሚያ ላይ እንዲደርሱ ካደረጓቸው ማስረጃዎች መካከል ጥቂቶቹን ይመረምራል።” ሮሜ 1:20ን አንብብ።