መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
“ብዙ ሰዎች ኢየሱስ በማቴዎስ 6:9 ላይ የተናገራቸውን ቃላት በሚገባ ያውቋቸዋል። [ጥቅሱን አንብብ።] ይሁንና ብዙዎች አምላክን ልክ እንደ አባት መቅረብ ይቻላል የሚለው ሐሳብ ይከብዳቸዋል። እርስዎ ወደ አምላክ መቅረብ የምንችለው እንዴት ነው ብለው ያስባሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት በሰማይ የሚኖረው አባታችን ስላሉት የተለያዩ ባሕርያት የሚናገር ከመሆኑም በላይ እሱን እንዴት ልናውቀው እንደምንችል ያብራራል።”
ንቁ! መስከረም 2008
“ከሞት በኋላ ሕይወት አለ የሚለው ሐሳብ በዘመናት ሁሉ ብዙዎችን ሲያከራክር ቆይቷል። እርስዎ ይህን በተመለከተ ምን ሐሳብ አለዎት? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] እዚህ ጥቅስ ላይ ኢዮብ ምን እንዳለ ልብ ይበሉ። [ኢዮብ 14:14, 15ን አንብብ።] እነዚህ ርዕሶች ከመቃብር ወጥቶ እንደገና መኖርን በሚመለከት መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ሐሳብ ይዘዋል።”
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
“ውሳኔ ማድረግ የሚጠይቁ አንገብጋቢ ሁኔታዎች ሲገጥሙን አስተማማኝ ምክር ማግኘት የምንችለው ከየት ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ምሳሌ 3:5, 6ን አንብብ።] ይህ ርዕስ፣ የምናደርገው ውሳኔ ሊያስከትል ስለሚችለው ውጤት አስቀድመን ማሰባችን አስተዋይነት እንደሆነ ጎላ አድርጎ ይናገራል።” በገጽ 8 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! መስከረም 2008
“በዛሬው ጊዜ በምድር ላይ ከሚታየው የምግብ እጥረት የተነሳ ሰዎች ሲሠቃዩ ማየት የአምላክ ዓላማ ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህን ችግር ለማስወገድ ሲል ምን ለማድረግ እንዳሰበ እስቲ ይመልከቱ። [መዝሙር 72:16ን አንብብ።] ይህ ርዕስ፣ አምላክ ገነትን በምድር ላይ መልሶ የሚያቋቁመው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።” በገጽ 7 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።