መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“አብዛኛው ሰው ስለ ሰላም ቢናገርም ዓለም አቀፍ አንድነት ግን ከሰው ልጆች ርቋል። ዓለም አቀፍ አንድነት ሕልም ብቻ ሆኖ የሚቀር ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ዓለምን አንድ ማድረግ የሚችል መንግሥት እንዳለ ይገልጻል።” መዝሙር 72:7, 8ን አንብብና ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ለመወያየት ተመልሰህ ለመምጣት ቀጠሮ ያዝ።
ንቁ! ሰኔ 2005
“ልጆች አስቸጋሪ በሆነው አፍላ የጉርምስና ዕድሜ የሚከሰቱትን ችግሮች ለማስወገድ እንዲችሉ ወላጆች እንዴት ሊረዷቸው የሚችሉ ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ኢሳይያስ 48:17, 18ን አንብብለት።] ይህ መጽሔት ወላጆች የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር በሥራ ላይ በማዋል ከልጆቻቸው ጋር ጥሩ የሐሳብ ግንኙነት ማድረግና አግባብነት ያላቸው ገደቦችን ማበጀት የሚችሉበትን መንገድ ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 15
“አብዛኞቻችን በሕይወታችን ውስጥ ሰፋ ያለውን ጊዜ የምናሳልፈው በሥራ ነው። አንዳንዶች ሥራን እንደ በረከት ሲያዩት ሌሎች ደግሞ እንደ እርግማን ይመለከቱታል። እርስዎስ ምን ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም መክብብ 2:24ን አንብብለት።] ይህ መጽሔት ለሥራ ሚዛናዊ የሆነ አመለካከት እንድናዳብር መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደሚረዳን ያሳያል። ከሥራ ጋር በተያያዘ የሚፈጠር ውጥረትን እንዴት መወጣት እንደሚቻልም ያብራራል።”