መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“ብዙውን ጊዜ ሰዎች የሚወዱትን ሰው በሞት ሲነጠቁ ወይም አንድ ዓይነት የጤና እክል ሲያጋጥማቸው ‘አምላክ ይህ እንዲደርስብኝ የፈቀደው ለምንድን ነው?’ ብለው ይጠይቃሉ። ምናልባት እርስዎም ተመሳሳይ ጥያቄ ይኖርዎት ይሆናል። አምላክ መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች ከልብ እንደሚያዝን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። [ኢሳይያስ 63:9ን የመጀመሪያውን ዓረፍተ ነገር አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክ ስቃይና መከራን እንደሚያስወግድ እርግጠኞች መሆን የምንችልበትን ምክንያት ያብራራል።”
ንቁ! ጥር 2003
“መንግሥታት የመናገር ነጻነትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ጣልቃ መግባት አለባቸው ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ የመናገር ነጻነት ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳደረገው [ሥራ 28:30, 31ን አንብብ።] ስለ ሃይማኖት ለሌሎች መስበክን የሚጨምር ከሆነስ? በቅርቡ ይህ ጉዳይ ለዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር። ይህን የፍርድ ጉዳይ በሚመለከት በዚህ የንቁ! እትም ላይ የወጣውን ሐሳብ እንዲያነቡ እንጋብዝዎታለን።”
መጠበቂያ ግንብ ጥር 15
“በዓለማችን ላይ የተፈጸሙትን ደም መፋሰሶች ሲመለከቱ ክፋት በምድር ላይ እንደነገሠና መልካም ነገር ከናካቴው እንደጠፋ ይሰማዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ አምላክን በሚመለከት ምን እንደሚል እዚህ ላይ ይመልከቱ። [መዝሙር 83:18 ሁለተኛውን ስንኝ አንብብ።] በምድር ሁሉ ላይ ልዑል የሆነው አምላክ ከሆነ ክፋት በእርግጥ ሊያሸንፍ ይችላል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ለዚህ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ይሰጣል።”
Jan. 22
“ዛሬ የምንኖረው ከምንጊዜውም ይበልጥ በደህንነታችን ላይ ስጋት ባጠላበት ዘመን ውስጥ ነው። ብዙዎች ገመናቸው ሳይቀር በሰዎች እየተደፈረ እንዳለ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይሰማዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ በደህንነታችን ላይ ስጋት የሚፈጥሩ ነገሮች ሙሉ በሙሉ እንደሚወገዱ ተስፋ ይሰጣል። [ኢሳይያስ 11:9ን አንብብ።] ይህ ተስፋ እንዴት እውን እንደሚሆን ይህ መጽሔት ያብራራል።”