መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“በዛሬው ጊዜ አንዳንዶች በአምላክ ላይ እምነት እያጡ ነው። ለዚህ አንዱ ምክንያት እንደሚከተሉት ላሉ ግራ የሚያጋቡ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ማግኘት አለመቻላቸው ነው። [በገጽ 6 ላይ ከሚገኘው ሣጥን አንድ ምሳሌ ጥቀስ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም በአምላክ ላይ ትክክለኛ እምነት እንዲኖረን የሚረዳ አንድ አስፈላጊ ነጥብ ያብራራል።” ፊልጵስዩስ 1:9ን አንብብ።
ንቁ! ታኅሣሥ 2003
“በዛሬው ጊዜ ፋሽን በብዙ ሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል። አንዳንዶች ለሰዎች አለባበስና ቁመና ከሚገባው በላይ ትኩረት እየተሰጠ እንዳለ ይሰማቸዋል። እርስዎ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት ስለ ፋሽን ሚዛናዊ አመለካከት እንዲኖረን ያበረታታል።” ቈላስይስ 3:12ን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 15
“ብዙ ሰዎች በሕይወታችን ውስጥ ልናከናውናቸው ከምንችላቸው በጣም አስፈላጊ ነገሮች አንዱ የቤተሰባችን ሕይወት የተሳካ እንዲሆን ማድረግ ነው ቢባል ይስማማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ የቤተሰብ ሕይወት ካሰፈረው ዘገባ ልንከተለው የሚገባ ግሩም ምሳሌ እናገኛለን። ኢየሱስ ያደገው በምን ዓይነት ቤተሰብ ውስጥ ይሆን ብለው አስበው ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ሉቃስ 2:51, 52ን አንብብ።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ስለ ኢየሱስ አስተዳደግ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሰፈረው ዘገባ ልናገኝ የምንችለውን ትምህርት ያብራራል።”
Dec. 22
ሁላችንም ልጆቻችን አስደሳችና አርኪ ሕይወት እንዲኖራቸው እንመኛለን። ልጆች በዓለም ላይ ያሉትን አስጨናቂ ሁኔታዎች ለመቋቋም እንዲችሉ በዋነኝነት የሚያስፈልጋቸው ነገር ምን ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ምሳሌ 22:6ን አንብብ።] ይህ የንቁ! እትም ልጆች የሚያስፈልጓቸውን ነገሮችና ወላጆች እነዚህን ነገሮች እንዴት ማሟላት እንደሚችሉ ያብራራል።”