መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“የሰው ልጆችን ከእንስሳት ልዩ ከሚያደርጓቸው ባሕርያት አንዱ ትክክልና ስህተት የሆነውን ለመለየት ያላቸው ችሎታ ነው። የሚያሳዝነው ግን ብዙ ሰዎች መጥፎ ነገሮችን ይፈጽማሉ። ይህ የሆነው ለምን ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ኤርምያስ 17:9ን ወይም ራእይ 12:9ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ትክክል የሆነውን ለማወቅና ያንን ለማድረግ የሚያስችለንን እርዳታ ከየት ማግኘት እንደምንችል ያብራራል።”
ንቁ! ታኅሣሥ 2004
“ልጆች በጊዜያችን የሚያጋጥሟቸውን ተጽዕኖዎች ለመቋቋም አመራር ያስፈልጋቸዋል ቢባል አይስማሙም? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ኤፌሶን 6:4ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ተግሣጽ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ በጥልቀት ይመረምራል። እንዲሁም ወላጆች ልጆቻቸውን ሳያስመርሩ መመሪያና እርማት መስጠት የሚችሉበትን መንገድ ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 15
“በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ ሰዎች በየዓመቱ በዚህ ወቅት የኢየሱስን ልደት በተለያዩ መንገዶች ያከብራሉ። የኢየሱስን መወለድ ከዘላለማዊ ሰላም ጋር አያይዞ የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት እንዳለ ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ኢሳይያስ 9:6, 7ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በጥቅሱ ላይ የተገለጸው ሰላም እንዴት እንደሚገኝ ያብራራል።”