መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“የአንድ ሰው ስኬት ባካበተው ሀብት የሚለካ ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም 1 ጢሞቴዎስ 6:9, 10ን አንብብ።] መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብ ማግኘትን የማያወግዝ ቢሆንም እውነተኛ ስኬት የተመካው በሀብት ላይ እንዳልሆነ ይጠቁማል። ይህ መጽሔት ስለዚህ ጉዳይ ማብራሪያ ይሰጣል።”
ንቁ! ጥር 2007
“ክርስቲያን ነን የሚሉ ብዙ ሰዎች የኢየሱስን ትምህርቶች እንደማይከተሉ ልብ ብለዋል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ለምሳሌ ያህል፣ ብዙዎች ኢየሱስ እዚህ ላይ የተናገራቸውን ቃላት በሥራ ላይ አያውሉም። [ዮሐንስ 13:35ን አንብብ።] ይህ ርዕሰ ጉዳይ ኢየሱስ ባስተማረው ትምህርትና ክርስቲያን ነን የሚሉ ብዙ ሰዎች ባላቸው አስተሳሰብ መካከል ያለውን ልዩነት በጥንቃቄ ይመረምራል።” በገጽ 18 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ጥር 15
“የትዳር ጓደኛሞች አስተማማኝ ምክር ማግኘት የሚችሉት ከየት ነው ብለው ያስባሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ጋብቻን ያቋቋመው ማን እንደሆነ እስቲ ይመልከቱ። [ዘፍጥረት 2:22ን አንብብ።] በተጨማሪም አምላክ ባልም ሆነ ሚስት ያላቸውን የተከበረ ቦታ በማስመልከት መመሪያዎችን ሰጥቷል። ይህ መጽሔት በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ይሰጣል።”
ንቁ! የካቲት 2007
“በአንዳንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ ሰዎች ለሃይማኖት ያላቸው አመለካከት እየተለወጠ የመጣ ይመስላል። አብያተ ክርስቲያናት የነበራቸውን ተቀባይነት በማጣት ላይ እንዳሉ ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ሐዋርያው ጳውሎስ የተናገራቸው የሚከተሉት ቃላት አንዳንዶች በሃይማኖት ላይ የነበራቸውን እምነት ያጡት ለምን እንደሆነ ግልጽ ያደርጋሉ። [የሐዋርያት ሥራ 20:29, 30ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የክርስትና የወደፊት ዕጣ ምን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ሐሳብ ይዟል።”