መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“ከአምላክ ቃል ላይ ጠቃሚ የሆነ አንድ ሐሳብ ባካፍልዎት ደስ ይለኛል። እዚህ ጥቅስ ላይ በተገለጸው ሐሳብ ይስማማሉ? [ያዕቆብ 3:2ን አንብብ።] ይህ ርዕስ የቤተሰባችንን አባላት በአነጋገራችን ከመጉዳት እንድንርቅ የሚረዱንን አንዳንድ ጠቃሚ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳቦችን ይዟል።” በገጽ 10 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ጥር 2008
“ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች መቋቋም እንዲችሉ ለመርዳት ጥረት እያደረግን ነው። ለምሳሌ ያህል፣ በየትኛውም ትዳር ውስጥ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ይኖራሉ። የትዳር ጓደኛሞች አስተማማኝ ምክር ማግኘት የሚችሉት ከየት ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህን ጠቃሚ መመሪያ ይመልከቱ። [ኤፌሶን 5:22, 25ን አንብብ።] ይህ ርዕስ ሚስት ለባሏ ትገዛለች ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ያብራራል።” በገጽ 28 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“በብዙዎች ዘንድ የሚታወቅ አንድ ጥቅስ ምን ትርጉም እንዳለው ከሰዎች ጋር እየተወያየን ነበር። በርካታ ሰዎች የአምላክ መንግሥት እንዲመጣ ይጸልያሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ ለተከታዮቹ ያስተማራቸውን ይህን ታዋቂ ጸሎት ይመልከቱ። [ማቴዎስ 6:9, 10ን አንብብ።] ‘የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? የሚመጣውስ መቼ ነው?’ ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል ያብራራል።”
ንቁ! ጥር 2008
“መለኮታዊ ጥበብ ያለውን የላቀ ጠቀሜታ በሚመለከት ከሰዎች ጋር እየተወያየን ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ በታሪክ ዘመናት ሁሉ ሴቶች መድልዎ ሲደረግባቸውና ጥቃት ሲፈጸምባቸው ቆይቷል። ይህ የሆነው ለምን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ ባሎች ሚስቶቻቸውን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የሚናገረውን ሐሳብ ይመልከቱ። [1 ጴጥሮስ 3:7ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክና ክርስቶስ ለሴቶች ያላቸውን አመለካከት ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሰ ያብራራል።”