መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“ለዚህ ጥያቄ ምን መልስ ይሰጣሉ? [በመጽሔቱ ሽፋን ላይ የሚገኘውን ጥያቄ አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] አምላክ የሰውን ዘር በሙሉ አንድ የማድረግ ዓላማ አለው። [መዝሙር 46:8, 9ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አንድነት ሊኖር የሚችልበትን መንገድ በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ያብራራል።”
ንቁ! ታኅሣሥ 2007
“በሞት የተለዩን የምንወዳቸው ሰዎች ዳግመኛ በሕይወት የሚኖሩበት ጊዜ ይመጣል ብለው አስበው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ ከሞት ማምለጥ የሚቻልበት መንገድ እንዳለ ይናገራል። [መዝሙር 68:20ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ሞት የሰው ልጆች መጨረሻ እንደሆነ አድርገን በመመልከት መፍራት የማይኖርብን ለምን እንደሆነ ይገልጻል።”
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 15
“በበዓል ወቅት በርካታ ሰዎች ደግነትና ርኅራኄ ለማሳየት ጥረት ያደርጋሉ። ሰዎች ከዓመት እስከ ዓመት ርኅራኄ ቢያሳዩ የዓለማችን ሁኔታ የተሻለ የሚሆን አይመስልዎትም? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም 1 ጴጥሮስ 3:8ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ርኅሩኅ መሆን ያለውን ጠቀሜታና ይህን ባሕርይ በተግባር ማሳየት የሚቻልባቸውን መንገዶች በተመለከተ ማብራሪያ ይሰጣል።”
ንቁ! ጥር 2008
“በታሪክ ዘመናት ሁሉ ሴቶች መድልዎ ሲደረግባቸውና ጥቃት ሲፈጸምባቸው ቆይቷል። ይህ የሆነው ለምን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ ባሎች ሚስቶቻቸውን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የሚናገረውን ሐሳብ ይመልከቱ። [1 ጴጥሮስ 3:7ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አምላክና ክርስቶስ ለሴቶች ያላቸውን አመለካከት ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሰ ያብራራል።”