መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1
“ብዙ ሰዎች ሰብዓዊ መሪዎች በጊዜያችን ላሉት ችግሮች መፍትሔ ማስገኘት ይችላሉ የሚል እምነት የላቸውም። በእነዚህ ጥቅሶች ላይ የተነገሩትን ትንቢቶች ለመፈጸም የሚችል መሪ ይኖራል ብለው ያስባሉ? [መዝሙር 72:7, 12, 16ን አንብብ። ከዚያም መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት በትንቢቱ ላይ የተጠቀሰውን መሪ ማንነትና ምን ነገሮችን እንደሚያከናውን ያብራራል።”
ንቁ! ኅዳር 2004
“በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ በሕይወት ዘመኑ ውስጥ በሆነ ወቅት ላይ በአእምሮ ሕመም እንደሚጠቃ ይገመታል። አብዛኞቻችን በበሽታው የሚሰቃይ የምናውቀው ሰው ይኖራል። [ርዕሱን ገልጠህ አሳየው።] ይህ ርዕስ የቤተሰባችን አባል ወይም በቅርብ የምናውቀው ሰው በእንዲህ ዓይነት ሕመም ቢጠቃ ምን ማድረግ እንደሚኖርብን የሚገልጹ ጠቃሚ ሐሳቦች ይዟል።”
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 15
“ብዙ ሰዎች ጥሩ ጤና አግኝተው ረጅም ዕድሜ መኖር ይፈልጋሉ። የሚቻል ቢሆን እርስዎስ ለዘላለም መኖር ይፈልጋሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን የዘላለም ሕይወት ተስፋ የሚያብራራ ሲሆን ይህ ተስፋ እውን ሲሆን ሕይወት ምን እንደሚመስልም ይጠቁማል።”