መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት በአሁኑ ጊዜ በመፈጸም ላይ እንዳለ ሆኖ ይሰማዎታል? [ማቴዎስ 24:11ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ስላላቸው አንዳንድ ትምህርቶች ይናገራል። በተጨማሪም ሐሰተኛ አስተማሪዎች እንዳያታልሉን እንዴት መጠንቀቅ እንደምንችል ይገልጻል።”
ንቁ! ታኅሣሥ 2006
“የአልኮል መጠጦችን በተመለከተ እርስ በርስ የሚጋጩ ሃይማኖታዊ አመለካከቶች ሲሰነዘሩ ይደመጣል። አምላክ የአልኮል መጠጦችን በተመለከተ ምን የሚሰማው ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] የኢየሱስ የመጀመሪያ ተአምር ውኃን ወደ ወይን መቀየር ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ የሚከተለውን ማስጠንቀቂያ ይሰጣል። [ምሳሌ 20:1ን አንብብ።] ይህ ርዕስ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ ያለውን ሚዛናዊ አመለካከት ያብራራል።” በገጽ 18 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 15
“በዚህ ወር ብዙ ሰዎች፣ መላእክት ኢየሱስ በተወለደበት ጊዜ በተናገሯቸው ቃላት ላይ ያሰላስላሉ። [ሉቃስ 2:14ን አንብብ።] ሰላም በምድር ላይ የሚሰፍንበት ጊዜ በእርግጥ እንደሚመጣ ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት፣ በቅርቡ ኢየሱስ በምድር ላይ እውነተኛ ሰላም የሚያመጣው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ጥር 2007
“ይህ ጥቅስ ሲፈጸም የምናይበት ጊዜ እንደሚመጣ ይሰማዎታል? [ኢሳይያስ 33:24ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት የሕክምና ሳይንስ ምን ውጤት እንዳገኘና የጠቀስነው የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ እንዴት እንደሚፈጸም ያብራራል።”