መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“ዛሬ ዛሬ በኢኮኖሚ ችግር የማይደቆስ የለም ለማለት ይቻላል። አብያተ ክርስቲያናትም በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ ሰዎች ገንዘብ እንዲያዋጡ የሚያደርጉት ውትወታ ጨምሯል። ይህ ሁኔታ ያስጨንቅዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም 1 ተሰሎንቄ 2:9ን አንብብ።] መጠበቂያ ግንብ የተባለው ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል ያብራራል።”
ንቁ! ታኅሣሥ 2002
“በአሁኑ ወቅት ሕይወት ለብዙዎች አስተማማኝ አይደለም። [መክብብ 9:11ን አንብብ።] እምነት የሚጣልበት መመሪያ ከየት የሚገኝ ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አንዳንዶች ስለ ወደፊት ሕይወታቸው ለማወቅ አውደ ነገሥትን ይመለከታሉ። በዚህ መንገድ ወደፊት ስለሚያጋጥምዎት ነገር በትክክል ማወቅ የሚቻል ይመስልዎታል? ስለ ወደፊቱ ጊዜ አስተማማኝ መመሪያ ከየት ሊያገኙ ይችላሉ? ንቁ! መጽሔት ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።”
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 15
“ብዙዎች በዓመቱ ውስጥ በዚህ ወቅት ላይ ስለ ኢየሱስ ልደት ያስባሉ። ስለ ኢየሱስ ልደት ከሚያወሳው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ብዙ ጠቃሚ ትምህርቶች ልናገኝ እንደምንችል ያውቃሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ከመጽሔቱ ላይ ገጽ 5ን አውጣና 2 ጢሞቴዎስ 3:16ን አንብብለት።] ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ከእነዚህ ትምህርቶች ውስጥ አንዳንዶቹን ይዟል።”
Dec. 22
“ወላጆች በጊዜያችን ያሉት ዓመፅን የሚያበረታቱ ጨዋታዎች በልጆቻችን ላይ መጥፎ ተጽዕኖ ያሳድራሉ ብለው እንዲሰጉ የሚያደርግ ሁኔታ ያለ አይመስልዎትም? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ብዙ ወላጆች የኤሌክትሮኒክ ጨዋታዎችን በተመለከተ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንደ መመሪያ አድርገው ይወስዳሉ። [መዝሙር 11:5ን አንብብ።] ይህ የንቁ! እትም ቤተሰቦች የኤሌክትሮኒክ ጨዋታዎች የሚያስከትሉትን ጉዳት ጠለቅ ብለው እንዲመረምሩ ይረዳቸዋል።”