መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ታኅ. 1
“ብዙ ሰዎች በዚህ ወቅት ስጦታ መለዋወጣቸውና ለሌሎች መልካም ነገር ማድረጋቸው የተለመደ ነው። ይህም ወርቃማውን ሕግ ያስታውሰናል። [ማቴዎስ 7:12ን አንብብ።] ዓመቱን ሙሉ በዚህ ሕግ መመራት የሚቻል ይመስልዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ‘ወርቃማው ሕግ ዛሬም ይሠራል?’ የሚለው ይህ መጽሔት ብዙ ቁም ነገሮችን ይዟል።”
ንቁ! ታኅ. 2001
“የምንኖረው ዓመፅ በተስፋፋበት ጊዜ ነው ቢባል ሳይስማሙ አይቀሩም። [መልስ ከሰጠ በኋላ 2 ጢሞቴዎስ 3:3ን አንብብ።] ብዙውን ጊዜ የ‘ጭካኔ’ ድርጊቶች በቤተሰብ ውስጥ እንኳን ሳይቀር ይፈጸማሉ። ‘ድብደባ ለሚፈጸምባቸው ሴቶች የሚሆን እርዳታ’ የሚለው ይህ ርዕስ ተስፋ ያዘለ መልእክት ይዟል። ሐሳቡን ሊያካፍሉት የሚችሉት ሰው ያውቁ ይሆናል።”
መጠበቂያ ግንብ ታኅ. 15
“በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑም አላመኑ አብዛኞቹ ሰዎች በዚህ ወቅት ስለ እሱ ማሰባቸው አይቀርም። አንዳንዶች በእውን የነበረ አካል አድርገው አይመለከቱትም። እርስዎስ ምን ይላሉ? [መልስ ከሰጠ በኋላ ማቴዎስ 16:15, 16ን አንብብ።] ኢየሱስ ዛሬም ሆነ ወደፊት ሕይወትዎን እንዴት እንደሚነካው ለማወቅ ስለ ‘እውነተኛው ኢየሱስ’ የሚናገረውን ይህንን ርዕስ ቢያነቡ እንደሚደሰቱ እርግጠኛ ነኝ።”
Dec. 22
“ከስጋት ነፃ የሆነ ሕይወት ለመምራት በጤና ላይ ጉዳት የማያስከትል አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ሊኖረን ይገባል ቢባል አይስማሙምን? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመናት ለሕዝቦቹ የገባውን ቃል ልብ ይበሉ። [ዘሌዋውያን 26:4, 5ን አንብብ።] ንቁ! ምግባችንን በተመለከተ ዛሬ ያሉትን አሳሳቢ ጉዳዮች ይገልጻል። እንዲሁም አምላክ ከስጋት ነፃ የሆነ ዓለም ስለሚያመጣበት ጊዜ ይናገራል።”