መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1
“ብዙ ሰዎች ዓለም ውስጥ ባለው የፍትሕ መዛባት ግራ ተጋብተዋል። ዓለምን መለወጥ የሚችል አንድ አካል ይኖራል ብለው አስበው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ለለውጥ እንቅፋት የሆኑትን ነገሮች ይመረምራል። በተጨማሪም እነዚህን እንቅፋቶች የሚያስወግደው ማን እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን ይህ አካል በዓለማችን ላይ እውነተኛ ሰላምና ደኅንነት እንዴት እንደሚያስገኝ ያስረዳል።” መዝሙር 72:12-14ን አንብብ።
ንቁ! ኅዳር 2005
“በዓለም ዙሪያ በሀብታሞችና በድሆች መካከል ሰፊ የኑሮ ልዩነት አለ። ይህን ልዩነት ለመድፈን የሚያስችል መፍትሔ ያለ ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ማቴዎስ 6:9, 10ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የአምላክ መንግሥት የኑሮ ልዩነት የፈጠረውን ችግር እንደሚያስወግድ እርግጠኞች እንድንሆን የሚያስችለንን ምክንያት ይገልጻል።”
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 15
“ብዙ ሰዎች ሰብዓዊውን ኅብረተሰብ የሚያስጨንቁት ችግሮች ከመሻሻል ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ የሚመጡበት ምክንያት ምን እንደሆነ ግራ ገብቷቸዋል። የዚህ ጥቅስ ሐሳብ አንደኛው ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አስበው ያውቃሉ? [ራእይ 12:9ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ዲያብሎስ ሰዎችን ለማሳት የሚጠቀምባቸውን ዘዴዎች ከመግለጹም በላይ የሚያሳድርብንን ተጽዕኖ እንዴት መቋቋም እንደምንችል ያስረዳል።”