መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 1
“ማንኛችንም ብንሆን በአንድ ወቅት ያመንነው ሰው ከድቶን ሊሆን ይችላል። ‘ልተማመንበት የምችል ሰው አለ?’ ብለው ጠይቀው ያውቃሉ። [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት። ከዚያም ምሳሌ 3:5ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በአምላክ ላይ ሙሉ በሙሉ መተማመን የምንችልበትን ምክንያት ያብራራል። ከዚህም በላይ እምነት ልንጥልባቸው የሚገቡ ሰዎችን እንዴት መምረጥ እንደምንችል ይገልጻል።”
ንቁ! ኀዳር 2003
“ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከአየር ጠባይ መዛባት ጋር በተያያዘ የተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ጉዳት አስከትለዋል። በዚህ ሳቢያ የሚከሰተውን ጉዳት ለመቀነስ ምን ቢደረግ ይሻላል ይላሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ይህ መጽሔት የአየር ጠባይ መለዋወጥ የሚያስከትለውን ችግር እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያቀርበውን መፍትሔ ያብራራል።”—ኢሳይያስ 35:1ን አንብብ።
መጠበቂያ ግንብ ኅዳር 15
“ቀደም ባሉት ዓመታት ብዙ ሰዎች ምድር ከጊዜ በኋላ ገነት እንደምትሆን ያምኑ ነበር። ዛሬ ግን አንዳንዶች ከጥፋት መትረፏ እንኳ አጠራጣሪ ሆኖባቸዋል። ወደፊት ምድር ምን ትሆናለች ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል ይመልከቱ። [መዝሙር 37:11ን አንብብ።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ምድር የወደፊት ሁኔታ የሚሰጠውን ሐሳብ ያብራራል።”
Nov. 22
“አንዳንዶች አካባቢያችን ሊስተካከል በማይችል መልኩ እንደተበላሸ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ሁኔታው ምንም ተስፋ እንደሌለው ይሰማዎታል? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ፈጣሪ ምድር ለመኖሪያነት የማትመች የቆሻሻ ማጠራቀሚያ እንድትሆን ዓላማው አልነበረም። [ኢሳይያስ 45:18ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ምድር ከጥፋት ልትተርፍ የምትችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”