መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት እንችላለን?
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1
“ሰዎች ስለዚህ ጥቅስ ያላቸውን አመለካከት እየጠየቅናቸው ነበር። [ማቴዎስ 5:10ን አንብብ።] አንድ ሰው እየተሰደደም እንዴት ደስተኛ ሊሆን ይችላል ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] የዚህ መጽሔት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ርዕሶች ስደትና መከራ እየደረሰባቸውም ደስተኛ መሆን ስለቻሉ ሰዎች ይናገራሉ። እነዚህ ሰዎች ደስተኛ መሆን የቻሉት እንዴት እንደሆነ ለማወቅ መጽሔቱን እንዲያነብቡ እንጋብዝዎታለን።”
ንቁ! መጋቢት 2003
“ይህ የንቁ! መጽሔት የጊዜያችን አሳዛኝ እውነታ ስለሆነው የልጆች ዝሙት አዳሪነት ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስ በልጆች ላይ የሚፈጸመው ይህ ግፍ የሚወገድበት ጊዜ ሩቅ እንዳልሆነ ተስፋ ይሰጣል። [ምሳሌ 2:21, 22ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ልጆችን ለዚህ አስከፊ ሕይወት የሚዳርጋቸው ምን እንደሆነና ወደፊት እንዴት እንደሚወገድ ይገልጻል።”
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 15
“የኢየሱስ ትምህርቶች ለጊዜያችን ጠቃሚ ናቸው ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] ኢየሱስ በሕይወቱ የመጨረሻ ቀን ላይ በሰጠው በዚህ ትእዛዝ እንደሚስማሙ አያጠራጥርም። [ዮሐንስ 15:12ን አንብብ።] በዚያ ዕለት ኢየሱስ ሌሎች ጠቃሚ ትምህርቶችንም አስተምሯል። ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ከእነዚህ ትምህርቶች እንዴት ጥቅም ማግኘት እንደምንችል ያብራራል።”
Mar. 8
“ሕይወት በችግር የተሞላ ቢሆንም ፈጣሪያችንን እንድናመሰግን የሚያደርጉን ብዙ ምክንያቶች አሉን ቢባል አይስማሙም? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አመስጋኝ የምንሆንበት አንዱ ምክንያት አፈጣጠራችን ነው። [መዝሙር 139:14ን አንብብ።] ሕይወትን ለማጣጣም የሚያስችሉን የስሜት ሕዋሳቶች ስላሉን አመስጋኞች መሆን እንዳለብን ይህ የንቁ! መጽሔት ያብራራል።”