መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1
“ብዙ ሰዎች ሃይማኖቶች ወደ አምላክ የሚያደርሱ የተለያዩ መንገዶች እንደሆኑ ይሰማቸዋል። አንድ ሰው የሚመርጠው ሃይማኖት ከአምላክ ጋር ባለው ግንኙነት ረገድ ለውጥ እንደሚያመጣ ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] እስቲ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ይመልከቱ። [1 ዮሐንስ 4:1ን አንብብ።] ይህ መጽሔት አንዳንድ ሃይማኖታዊ ትምህርቶች ከአምላክ የመጡ መሆን አለመሆናቸውን መመርመር የምንችልባቸውን መንገዶች ይጠቁመናል፤ እንዲሁም የተለያዩ ሃይማኖቶች እንዴት እንደጀመሩ ያብራራል።”
ንቁ! መጋቢት 2007
“ዝነኛ የሆኑ በርካታ ሰዎች የኩራት ባሕርይ ይታይባቸዋል። ይህ ባሕርይ በዓለም ላይ ሰላምና ደስታ ለማስፈን የሚረዳ ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ ኩራትን ወይም እብሪትን አስመልክቶ ምን እንደሚል ይመልከቱ። [ምሳሌ 16:18ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ትሑት መሆን የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች ይገልጻል።” በገጽ 20 ላይ ያለውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 15
“ሰዎች ስለ ክርስቶስ መምጣት ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው። በእርስዎ አመለካከት ይህ ሁኔታ በጉጉት የሚጠበቅ ነው ወይስ የሚያስፈራ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ የሆነው ሐዋርያው ዮሐንስ ይህን ሁኔታ በተመለከተ ምን እንደተሰማው ይመልከቱ። [ራእይ 22:20ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የክርስቶስ መምጣት ምን እንደሚያከናውን ያብራራል።”
ንቁ! ሚያዝያ 2007
“በበርካታ የዓለማችን ክፍሎች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሥነ ምግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ እንደመጣ ይሰማቸዋል። እርስዎስ እንደዚያ ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ዛሬ የምናያቸው እነዚህ ሁኔታዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኝ አንድ ትንቢት ፍጻሜ ናቸው። [2 ጢሞቴዎስ 3:2-4ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የሥነ ምግባር ማሽቆልቆል ሲባል ምን ማለት እንደሆነና ይህ ሁኔታ የሰውን ዘር ወዴት እየመራው እንዳለም ያብራራል።”