የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/08 ገጽ 6
  • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 3/08 ገጽ 6

መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት

መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1

“በዛሬው ጊዜ በርካታ ችግሮች እያሉም እንኳ እውነተኛ የአእምሮ ሰላም ማግኘት የሚቻል ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱን ጊዜ አስመልክቶ የሚሰጠውን ተስፋ ማወቃቸው የአእምሮ ሰላም እንዲያገኙ አስችሏቸዋል። [በምታስተዋውቀው ርዕስ ውስጥ ከሚገኙት ጥቅሶች መካከል አንዱን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ ወደ ሕልውና ስለመጣንበት መንገድ፣ ስለ ሕይወት ዓላማና ስለ ወደፊቱ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ያብራራል።”

ንቁ! የካቲት 2008

“ወንጀል በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ብዙ ሰዎች የደኅንነት ስሜት አይሰማቸውም። ወደፊት እነዚህ ሁኔታዎች ይሻሻላሉ ብለው አስበው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰ አንድ አስደሳች ትንቢት ይመልከቱ። [መዝሙር 37:10ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ የወንጀል ዋነኛ መንስኤ ምን እንደሆነና መፍትሔውን በሚመለከት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል የሚገልጽ ማብራሪያ ይዟል።”

መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1

“ቤተሰቦች እዚህ ጥቅስ ላይ ያለውን ሐሳብ ተግባራዊ ቢያደርጉ ምን ዓይነት ሁኔታ የሚፈጠር ይመስልዎታል? [ኤፌሶን 4:31ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ ርዕስ ግጭቶችን ለመፍታትና ትዳር ደስታ የሰፈነበት እንዲሆን ለማድረግ የሚረዱ ጠቃሚ ሐሳቦችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያብራራል።” በገጽ 18 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።

ንቁ! የካቲት 2008

“አንዳንዶች አምላክ የምንሠራውን እያንዳንዱን ስህተት ይከታተላል የሚል እምነት አላቸው። ሌሎች ደግሞ ሁኔታው ምንም ያህል ከባድ ቢሆን አምላክ ሁሉንም ኃጢአት ይቅር እንደሚል ይሰማቸዋል። እርስዎ ምን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም የሐዋርያት ሥራ 3:19ን አንብብ።] ይህ ርዕስ የአምላክን ምሕረት ለማግኘት የሚያስችሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ሦስት እርምጃዎችን ያብራራል።” በገጽ 10 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ