መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1
“እያንዳንዱ ሰው እዚህ ጥቅስ ላይ የሚገኘውን ምክር ቢከተል በአካባቢያችን የተሻለ ሁኔታ እንደሚሰፍን አይሰማዎትም? [ኤፌሶን 4:25ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ብዙ ሰዎች መዋሸት ጥሩ የሚሆንባቸው አጋጣሚዎች እንዳሉ ይሰማቸዋል። ይህ መጽሔት ሁልጊዜ እውነቱን መናገር ምን ጥቅም እንዳለው ያብራራል።”
ንቁ! የካቲት 2007
“ዛሬ በዓለማችን ላይ ለምናየው ችግር ሁሉ መንስኤው እዚህ ጥቅስ ላይ የተጠቀሰው አካል አይመስልዎትም? [1 ዮሐንስ 5:19ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ‘ስለ ክፉው’ ማንነት የሚናገረውን ሐሳብ የያዘ ሲሆን እርሱ ከሚያሳድረው ኃይለኛ ተጽዕኖ ራሳችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት እንደሆነም ያብራራል።” ገጽ 12 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አሳየው።
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 15
“አንዳንዶች የሰው ልጆች ምድርን እያበላሿት እንደሆነ ይሰማቸዋል። ይህ ጉዳይ እርስዎንስ አሳስብዎት አያውቅም? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] እስቲ ይህን አስደሳች ተስፋ ይመልከቱ። [ራእይ 11:18ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ምድራችንን ልዩ የሚያደርጋት ምን እንደሆነ የሚያብራራ ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ የምድርን የወደፊት ሁኔታ አስመልክቶ የሚናገረውን ሐሳብም ይዟል።”
ንቁ! መጋቢት 2007
“ዛሬ ያሉ ወጣቶች ምን ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ያጋጥሟቸዋል ብለው ያስባሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ወጣቶች ከሚያጋጥሟቸው ችግሮች መካከል አንዱን ይኸውም ጥሩ ጓደኛ የማግኘትን ችግር በተመለከተ ይናገራል። [ምሳሌ 13:20ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በኢንተርኔት አማካኝነት ጓደኛ ለማፍራት መሞከር የሚያስከትለውን አደጋና ወጣቶች ከዚህ አደጋ ራሳቸውን መጠበቅ እንዲችሉ መርዳት የሚቻልበትን መንገድ ያብራራል።”